-
ዘፀአት 4:14-16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቁጣ በሙሴ ላይ ነደደ፤ እንዲህም አለው፦ “እሺ ሌዋዊው ወንድምህ አሮንስ?+ እሱ በደንብ መናገር እንደሚችል አውቃለሁ። ደግሞም አንተን ለማግኘት አሁን ወደዚህ እየመጣ ነው። በሚያይህም ጊዜ ልቡ በደስታ ይሞላል።+ 15 ስለሆነም እሱን አነጋግረው፤ ቃላቱንም በአንደበቱ አኑር፤+ በምትናገሩበትም ጊዜ ከአንተና ከእሱ ጋር እሆናለሁ፤+ ምን ማድረግ እንዳለባችሁም አስተምራችኋለሁ። 16 እሱም አንተን ወክሎ ለሕዝቡ ይናገራል፤ እንደ ቃል አቀባይም ይሆንልሃል፤ አንተም ለእሱ እንደ አምላክ ትሆናለህ።*+
-
-
ዘፀአት 4:30አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 አሮንም ይሖዋ ለሙሴ የነገረውን ቃል ሁሉ ነገራቸው፤ እሱም በሕዝቡ ፊት ተአምራዊ ምልክቶቹን አደረገ።+
-
-
ዘፀአት 15:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 ከዚያም የአሮን እህት ነቢዪቱ ሚርያም አታሞ አነሳች፤ ሴቶቹም ሁሉ አታሞ እየመቱና እየጨፈሩ ተከተሏት።
-