ዘፀአት 32:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ይሖዋም በመቀጠል ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ ግትር* መሆኑን ተመልክቻለሁ።+ 10 እንግዲህ አሁን ቁጣዬ እንዲነድባቸውና እንዳጠፋቸው ተወኝ፤ አንተን በእነሱ ምትክ ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ።”+ ዘኁልቁ 25:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ስለዚህ እስራኤል የፌጎርን ባአል በማምለክ ተባበረ፤*+ ይሖዋም በእስራኤል ላይ እጅግ ተቆጣ። ዘዳግም 11:16, 17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ልባችሁ እንዳይታለልና ዞር ብላችሁ ሌሎች አማልክትን እንዳታመልኩ እንዲሁም እንዳትሰግዱላቸው ተጠንቀቁ።+ 17 አለዚያ የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ይነድዳል፤ ዝናብ ዘንቦ ምድሪቱ ምርት እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤+ እናንተም ይሖዋ ከሚሰጣችሁ መልካም ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።+ መሳፍንት 2:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ በመሆኑም ለሚዘርፏቸው ዘራፊዎች አሳልፎ ሰጣቸው።+ በዙሪያቸው ላሉ ጠላቶቻቸው ሸጣቸው፤+ ከዚያ ወዲህ ጠላቶቻቸውን መቋቋም አልቻሉም።+
9 ይሖዋም በመቀጠል ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ ግትር* መሆኑን ተመልክቻለሁ።+ 10 እንግዲህ አሁን ቁጣዬ እንዲነድባቸውና እንዳጠፋቸው ተወኝ፤ አንተን በእነሱ ምትክ ታላቅ ብሔር አደርግሃለሁ።”+
16 ልባችሁ እንዳይታለልና ዞር ብላችሁ ሌሎች አማልክትን እንዳታመልኩ እንዲሁም እንዳትሰግዱላቸው ተጠንቀቁ።+ 17 አለዚያ የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ይነድዳል፤ ዝናብ ዘንቦ ምድሪቱ ምርት እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤+ እናንተም ይሖዋ ከሚሰጣችሁ መልካም ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።+
14 በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ በመሆኑም ለሚዘርፏቸው ዘራፊዎች አሳልፎ ሰጣቸው።+ በዙሪያቸው ላሉ ጠላቶቻቸው ሸጣቸው፤+ ከዚያ ወዲህ ጠላቶቻቸውን መቋቋም አልቻሉም።+