ዘዳግም 3:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ስለ እናንተ የሚዋጋው+ አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆነ አትፍሯቸው።’ ዘዳግም 31:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ደፋርና ብርቱ ሁኑ።+ ከእናንተ ጋር የሚሄደው አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆነ አትፍሯቸው ወይም በፊታቸው አትሸበሩ።+ እሱ አይጥላችሁም ወይም አይተዋችሁም።”+ መዝሙር 20:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አንዳንዶች በሠረገሎች፣ ሌሎች ደግሞ በፈረሶች ይታመናሉ፤+እኛ ግን የአምላካችንን የይሖዋን ስም እንጠራለን።+ ምሳሌ 21:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤+መዳን ግን ከይሖዋ ዘንድ ነው።+