ዘኁልቁ 30:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 አንድ ሰው ለይሖዋ ስእለት ቢሳል+ ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ ራሱን* ግዴታ ውስጥ ቢያስገባ+ ቃሉን ማጠፍ የለበትም።+ አደርገዋለሁ ብሎ የማለውን ነገር ሁሉ መፈጸም አለበት።+ መዝሙር 15:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ነውረኛ የሆነን ሰው ሁሉ ይንቃል፤+ይሖዋን የሚፈሩትን ግን ያከብራል። ጉዳት ላይ ሊጥለው ቢችልም እንኳ ቃሉን* አያጥፍም።+ ምሳሌ 20:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ሰው ቸኩሎ “የተቀደሰ ነው!”+ ቢልና ከተሳለ በኋላ ስእለቱን መልሶ ማጤን ቢጀምር ወጥመድ ይሆንበታል።+
2 አንድ ሰው ለይሖዋ ስእለት ቢሳል+ ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ ራሱን* ግዴታ ውስጥ ቢያስገባ+ ቃሉን ማጠፍ የለበትም።+ አደርገዋለሁ ብሎ የማለውን ነገር ሁሉ መፈጸም አለበት።+