8 በማግስቱ ፍልስጤማውያን የሞቱትን ሰዎች ልብስና ትጥቅ ለመግፈፍ ሲመጡ ሳኦልንና ሦስቱን ወንዶች ልጆቹን በጊልቦአ+ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው። 9 ስለሆነም የሳኦልን ራስ ከቆረጡና የጦር ትጥቁን ከገፈፉ በኋላ ወሬው በጣዖቶቻቸው+ ቤቶችና በሕዝቡ ሁሉ መካከል እንዲሰራጭ+ ለማድረግ በመላው የፍልስጤም ምድር መልእክት ላኩ። 10 ከዚያም የጦር ትጥቁን በአስታሮት ምስሎች ቤት አስቀመጡት፣ አስከሬኑን ደግሞ በቤትሻን+ ግንብ ላይ ቸነከሩት።