የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 10:10-14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 እንግዲህ ይሖዋ በአክዓብ ቤት ላይ ከተናገረው የይሖዋ ቃል አንዱም እንኳ ሳይፈጸም እንደማይቀር* እወቁ፤+ ይሖዋ በአገልጋዩ በኤልያስ አማካኝነት የተናገረውን ቃል ፈጽሟል።”+ 11 በተጨማሪም ኢዩ በኢይዝራኤል ከአክዓብ ቤት የቀሩትን ሁሉ እንዲሁም ታዋቂ የሆኑ ሰዎቹን፣ ወዳጆቹንና ካህናቱን አንድም ሳያስቀር ገደላቸው።+

      12 ከዚያም ተነስቶ ወደ ሰማርያ አቀና። በመንገዱ ላይም የእረኞች ማቆያ ቤት* ይገኝ ነበር። 13 በዚያም ኢዩ የይሁዳን ንጉሥ የአካዝያስን+ ወንድሞች አገኛቸው፤ እሱም “እናንተ እነማን ናችሁ?” ሲላቸው “እኛ የአካዝያስ ወንድሞች ነን፤ የንጉሡን ልጆችና የንጉሡን እናት* ልጆች ደህንነት ለመጠየቅ እየወረድን ነው” አሉት። 14 እሱም ወዲያውኑ “በሕይወት እንዳሉ ያዟቸው!” አለ። በመሆኑም በሕይወት እንዳሉ ያዟቸው፤ በእረኞች ማቆያው ቤት አጠገብ በሚገኘው የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ 42ቱን ሰዎች አረዷቸው። ከመካከላቸው አንድም ሰው አላስተረፈም።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ