2 ሳሙኤል 7:12, 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ+ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ከአብራክህ የሚወጣውን ዘርህን አስነሳለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።+ 13 ለስሜ የሚሆን ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው፤+ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ።+ 1 ነገሥት 15:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ሆኖም በዳዊት+ የተነሳ አምላኩ ይሖዋ ከእሱ በኋላ ልጁን በማስነሳትና ኢየሩሳሌም ጸንታ እንድትኖር በማድረግ በኢየሩሳሌም መብራት ሰጠው።+ 2 ዜና መዋዕል 21:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ሆኖም ይሖዋ ከዳዊት ጋር ለገባው ቃል ኪዳን ሲል የዳዊትን ቤት ማጥፋት አልፈለገም፤+ ምክንያቱም ለእሱና ለልጆቹ ለሁልጊዜ የሚኖር መብራት* እንደሚሰጥ ቃል ገብቶ ነበር።+
12 የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ+ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ከአብራክህ የሚወጣውን ዘርህን አስነሳለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።+ 13 ለስሜ የሚሆን ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው፤+ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ።+
7 ሆኖም ይሖዋ ከዳዊት ጋር ለገባው ቃል ኪዳን ሲል የዳዊትን ቤት ማጥፋት አልፈለገም፤+ ምክንያቱም ለእሱና ለልጆቹ ለሁልጊዜ የሚኖር መብራት* እንደሚሰጥ ቃል ገብቶ ነበር።+