ዘፀአት 14:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ሰነዘረ፤+ ይሖዋም ሌሊቱን ሙሉ ኃይለኛ የምሥራቅ ነፋስ በማምጣት ባሕሩ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ፤ የባሕሩንም ወለል ወደ ደረቅ መሬት ለወጠው፤+ ውኃውም ተከፈለ።+ ኢያሱ 3:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ከላይ ይወርድ የነበረው ውኃ ቆመ። ውኃውም በሩቅ ይኸውም በጻረታን አጠገብ በምትገኘው በአዳም ከተማ እንደ ግድብ* ተቆልሎ ቆመ፤ በአረባ ወደሚገኘው ባሕር ይኸውም ወደ ጨው ባሕር* የሚወርደውም ውኃ ደረቀ። ውኃው ተቋርጦ ስለነበር ሕዝቡ ከኢያሪኮ ማዶ ወዳለው ስፍራ ተሻገረ። መዝሙር 114:1-3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 114 እስራኤል ከግብፅ ሲወጣ፣+የያዕቆብ ቤት ባዕድ ቋንቋ ከሚናገር ሕዝብ ተለይቶ ሲሄድ፣ 2 ይሁዳ መቅደሱ፣*እስራኤልም ግዛቱ ሆነ።+ 3 ባሕሩ ይህን አይቶ ሸሸ፤+ዮርዳኖስ ወደ ኋላ ተመለሰ።+
21 ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ሰነዘረ፤+ ይሖዋም ሌሊቱን ሙሉ ኃይለኛ የምሥራቅ ነፋስ በማምጣት ባሕሩ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ፤ የባሕሩንም ወለል ወደ ደረቅ መሬት ለወጠው፤+ ውኃውም ተከፈለ።+
16 ከላይ ይወርድ የነበረው ውኃ ቆመ። ውኃውም በሩቅ ይኸውም በጻረታን አጠገብ በምትገኘው በአዳም ከተማ እንደ ግድብ* ተቆልሎ ቆመ፤ በአረባ ወደሚገኘው ባሕር ይኸውም ወደ ጨው ባሕር* የሚወርደውም ውኃ ደረቀ። ውኃው ተቋርጦ ስለነበር ሕዝቡ ከኢያሪኮ ማዶ ወዳለው ስፍራ ተሻገረ።
114 እስራኤል ከግብፅ ሲወጣ፣+የያዕቆብ ቤት ባዕድ ቋንቋ ከሚናገር ሕዝብ ተለይቶ ሲሄድ፣ 2 ይሁዳ መቅደሱ፣*እስራኤልም ግዛቱ ሆነ።+ 3 ባሕሩ ይህን አይቶ ሸሸ፤+ዮርዳኖስ ወደ ኋላ ተመለሰ።+