8 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“ሞገስ በማሳይበት ዘመን መልስ ሰጥቼሃለሁ፤+
በመዳንም ቀን ረድቼሃለሁ፤+
ለሰዎች ቃል ኪዳን አድርጌ እሰጥህ ዘንድ ጠብቄሃለሁ፤+
ይህም ምድሪቱን ዳግመኛ እንድታቋቁም፣
የወደመውን ርስታቸውን መልሰህ እንድታወርሳቸው፣+
9 እስረኞቹን ‘ኑ ውጡ!’+
በጨለማ ያሉትንም+ ‘ራሳችሁን ግለጡ!’ እንድትል ነው።
በየመንገዱ ዳር ይመገባሉ፤
በተበላሹ መንገዶችም ሁሉ አጠገብ መሰማሪያ ያገኛሉ።