2 ሳሙኤል 20:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 በዚህ ጊዜ የቢንያማዊው የቢክሪ ልጅ የሆነ ሳባ+ የሚባል አንድ አስቸጋሪ ሰው ነበር። እሱም ቀንደ መለከት በመንፋት+ “እኛ ከዳዊት ጋር ምንም ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ጋር ምንም ውርሻ የለንም።+ እስራኤል ሆይ፣ እያንዳንድህ ወደ አማልክትህ* ተመለስ!” አለ።+ 2 ሳሙኤል 22:5, 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 የሞት ማዕበል ዙሪያዬን ከቦኛል፤+የማይረቡ ሰዎች የለቀቁት ድንገተኛ ጎርፍ አሸበረኝ።+ 6 የመቃብር* ገመድ ተጠመጠመብኝ፤+የሞት ወጥመድ ተጋረጠብኝ።+ መዝሙር 22:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ውሾች ከበውኛልና፤+እንደ ክፉ አድራጊዎች ሸንጎ በዙሪያዬ ሰፍረዋል፤+እንደ አንበሳ ሆነው እጆቼና እግሮቼ ላይ ተረባረቡ።*+
20 በዚህ ጊዜ የቢንያማዊው የቢክሪ ልጅ የሆነ ሳባ+ የሚባል አንድ አስቸጋሪ ሰው ነበር። እሱም ቀንደ መለከት በመንፋት+ “እኛ ከዳዊት ጋር ምንም ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ጋር ምንም ውርሻ የለንም።+ እስራኤል ሆይ፣ እያንዳንድህ ወደ አማልክትህ* ተመለስ!” አለ።+