መዝሙር 49:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ጥበበኞች እንኳ ሲሞቱ ያያል፤ሞኞችና ማመዛዘን የሚጎድላቸው ሰዎች አብረው ይጠፋሉ፤+ሀብታቸውንም ለሌሎች ትተውት ያልፋሉ።+ መክብብ 2:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ከኋላዬ ለሚመጣው ሰው ትቼው ስለምሄድ+ ከፀሐይ በታች እጅግ የደከምኩበትን ሥራ ሁሉ+ ጠላሁ። 19 ጥበበኛ ወይም ሞኝ እንደሚሆን የሚያውቅ ማን ነው?+ ሆኖም ከፀሐይ በታች በድካሜና በጥበቤ ያፈራሁትን ነገር ሁሉ ይወርሰዋል። ይህም ቢሆን ከንቱ ነው። መክብብ 4:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ብቸኛ የሆነና ጓደኛ የሌለው ሰው አለ፤ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ይሁንና የሚሠራው ሥራ ማብቂያ የለውም። ዓይኖቹ ሀብትን አይጠግቡም።+ ሆኖም ‘እንዲህ በትጋት የምሠራውና ራሴን* መልካም ነገር የምነፍገው ለማን ብዬ ነው?’ ብሎ ራሱን ይጠይቃል?+ ይህም ቢሆን ከንቱና አሰልቺ ሥራ ነው።+ ሉቃስ 12:19, 20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ነፍሴንም* “ነፍሴ* ሆይ፣ ለብዙ ዘመን የሚበቃ የተከማቸ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ዘና በይ፣ ብዪ፣ ጠጪ፣ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’ 20 አምላክ ግን ‘አንተ ማስተዋል የጎደለህ፣ በዚህች ሌሊት ሕይወትህን* ይፈልጓታል። ታዲያ ያከማቸኸው ነገር ለማን ይሆናል?’ አለው።+
18 ከኋላዬ ለሚመጣው ሰው ትቼው ስለምሄድ+ ከፀሐይ በታች እጅግ የደከምኩበትን ሥራ ሁሉ+ ጠላሁ። 19 ጥበበኛ ወይም ሞኝ እንደሚሆን የሚያውቅ ማን ነው?+ ሆኖም ከፀሐይ በታች በድካሜና በጥበቤ ያፈራሁትን ነገር ሁሉ ይወርሰዋል። ይህም ቢሆን ከንቱ ነው።
8 ብቸኛ የሆነና ጓደኛ የሌለው ሰው አለ፤ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ይሁንና የሚሠራው ሥራ ማብቂያ የለውም። ዓይኖቹ ሀብትን አይጠግቡም።+ ሆኖም ‘እንዲህ በትጋት የምሠራውና ራሴን* መልካም ነገር የምነፍገው ለማን ብዬ ነው?’ ብሎ ራሱን ይጠይቃል?+ ይህም ቢሆን ከንቱና አሰልቺ ሥራ ነው።+
19 ነፍሴንም* “ነፍሴ* ሆይ፣ ለብዙ ዘመን የሚበቃ የተከማቸ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ዘና በይ፣ ብዪ፣ ጠጪ፣ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’ 20 አምላክ ግን ‘አንተ ማስተዋል የጎደለህ፣ በዚህች ሌሊት ሕይወትህን* ይፈልጓታል። ታዲያ ያከማቸኸው ነገር ለማን ይሆናል?’ አለው።+