መዝሙር 39:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በእርግጥም ሰው ሁሉ የሚመላለሰው እንደ ጥላ ነው። ላይ ታች የሚለው* በከንቱ ነው። ማን እንደሚጠቀምበት ሳያውቅ ንብረት ያከማቻል።+ ምሳሌ 11:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በቁጣ ቀን ሀብት ፋይዳ አይኖረውም፤*+ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል።+ ምሳሌ 23:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ሀብት ለማግኘት አትልፋ።+ ይህን ትተህ በማስተዋል ተመላለስ።* መክብብ 2:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ከኋላዬ ለሚመጣው ሰው ትቼው ስለምሄድ+ ከፀሐይ በታች እጅግ የደከምኩበትን ሥራ ሁሉ+ ጠላሁ። ሉቃስ 12:19, 20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ነፍሴንም* “ነፍሴ* ሆይ፣ ለብዙ ዘመን የሚበቃ የተከማቸ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ዘና በይ፣ ብዪ፣ ጠጪ፣ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’ 20 አምላክ ግን ‘አንተ ማስተዋል የጎደለህ፣ በዚህች ሌሊት ሕይወትህን* ይፈልጓታል። ታዲያ ያከማቸኸው ነገር ለማን ይሆናል?’ አለው።+
19 ነፍሴንም* “ነፍሴ* ሆይ፣ ለብዙ ዘመን የሚበቃ የተከማቸ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ዘና በይ፣ ብዪ፣ ጠጪ፣ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’ 20 አምላክ ግን ‘አንተ ማስተዋል የጎደለህ፣ በዚህች ሌሊት ሕይወትህን* ይፈልጓታል። ታዲያ ያከማቸኸው ነገር ለማን ይሆናል?’ አለው።+