ምሳሌ 5:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 የጋጠወጥ* ሴት ከንፈር እንደ ማር እንጀራ ያንጠባጥባልና፤+አፏም ከዘይት ይለሰልሳል።+ ምሳሌ 7:4, 5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ጥበብን “እህቴ ነሽ” በላት፤ ማስተዋልንም “ዘመዴ” ብለህ ጥራት፤ 5 ጋጠወጥና*+ ባለጌ* ከሆነች ሴት፣እንዲሁም ከምትናገረው የሚያባብል* ቃል ይጠብቁሃል።+