ምሳሌ
7 ልጄ ሆይ፣ ቃሌን ጠብቅ፤
ትእዛዛቴንም እንደ ውድ ሀብት ያዝ።+
3 በጣቶችህ ላይ እሰራቸው፤
በልብህ ጽላት ላይ ጻፋቸው።+
4 ጥበብን “እህቴ ነሽ” በላት፤
ማስተዋልንም “ዘመዴ” ብለህ ጥራት፤
11 ሴትየዋ ጯኺና ማን አለብኝ ባይ ነች።+
ፈጽሞ ቤቷ አትቀመጥም።*
12 አንዴ በመንገድ፣ አንዴ በአደባባይ ትታያለች፤
በየመንገዱ መታጠፊያም ታደባለች።+
13 አፈፍ አድርጋ ይዛ ሳመችው፤
ያላንዳች ኀፍረትም እንዲህ አለችው፦
14 “የኅብረት መሥዋዕት ማቅረብ ነበረብኝ።+
ዛሬ ስእለቴን ፈጽሜአለሁ።
15 አንተን ለማግኘት የወጣሁት ለዚህ ነው፤
አንተን ፍለጋ ወጣሁ፤ ደግሞም አገኘሁህ!
16 መኝታዬን ባማረ የአልጋ ልብስ፣
ከግብፅ በመጣ በቀለማት ያሸበረቀ በፍታ አስጊጬዋለሁ።+
17 አልጋዬ ላይ ከርቤ፣ እሬትና* ቀረፋ አርከፍክፌአለሁ።+
18 ና፣ እስኪነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ፤
እርስ በርሳችን ፍቅራችንን በመግለጽ እንደሰት፤
19 ባሌ ቤት የለምና፤
ወደ ሩቅ ቦታ ሄዷል።
20 በከረጢት ገንዘብ ይዟል፤
ደግሞም ጨረቃዋ ሙሉ እስክትሆን ድረስ ወደ ቤት አይመለስም።”
21 እንደ ምንም ብላ አግባብታ ታሳስተዋለች።+
በለሰለሰ አንደበቷ ታታልለዋለች።
22 ለእርድ እንደሚነዳ በሬ፣
ለቅጣትም በእግር ግንድ* እንደታሰረ ሞኝ ሰው በድንገት ይከተላታል፤+
23 ፍላጻ ጉበቱን እስኪሰነጥቀው ድረስ፣
በወጥመድ ለመያዝ እንደምትቸኩል ወፍ ተከትሏት ይሄዳል፤ ሕይወቱን* ሊያሳጣው እንደሚችል አላወቀም።+
24 እንግዲህ ልጆቼ ሆይ፣ አዳምጡኝ፤
የምናገረውንም ቃል በትኩረት ስሙ።
25 ልባችሁን ወደ መንገዷ አታዘንብሉ።