ምሳሌ 5:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 የጋጠወጥ* ሴት ከንፈር እንደ ማር እንጀራ ያንጠባጥባልና፤+አፏም ከዘይት ይለሰልሳል።+ ምሳሌ 5:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 በመላው ጉባኤ መካከል*ሙሉ በሙሉ ልጠፋ ምንም አልቀረኝም ነበር።”+ ምሳሌ 7:22, 23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ለእርድ እንደሚነዳ በሬ፣ለቅጣትም በእግር ግንድ* እንደታሰረ ሞኝ ሰው በድንገት ይከተላታል፤+23 ፍላጻ ጉበቱን እስኪሰነጥቀው ድረስ፣በወጥመድ ለመያዝ እንደምትቸኩል ወፍ ተከትሏት ይሄዳል፤ ሕይወቱን* ሊያሳጣው እንደሚችል አላወቀም።+ ምሳሌ 22:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 የጋጠወጥ* ሴት አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው።+ ይሖዋ ያወገዘው ሰው እዚያ ውስጥ ይወድቃል።
22 ለእርድ እንደሚነዳ በሬ፣ለቅጣትም በእግር ግንድ* እንደታሰረ ሞኝ ሰው በድንገት ይከተላታል፤+23 ፍላጻ ጉበቱን እስኪሰነጥቀው ድረስ፣በወጥመድ ለመያዝ እንደምትቸኩል ወፍ ተከትሏት ይሄዳል፤ ሕይወቱን* ሊያሳጣው እንደሚችል አላወቀም።+