2 ዜና መዋዕል 36:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ለሕዝቡና ለማደሪያው ስፍራ ስለራራ መልእክተኞቹን እየላከ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 16 እነሱ ግን የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነድና+ ፈውስ እስከማይገኝላቸው ድረስ በእውነተኛው አምላክ መልእክተኞች ላይ ያላግጡ፣+ ቃሉን ይንቁና+ በነቢያቱ ላይ ያፌዙ+ ነበር። ኢሳይያስ 42:24, 25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ያዕቆብን ለዘረፋ፣እስራኤልንም ለበዝባዦች አሳልፎ የሰጠ ማን ነው? በእሱ ላይ ኃጢአት በመፈጸም የበደልነው ይሖዋ አይደለም? እነሱ በመንገዱ ለመሄድ አልፈለጉም፤ሕጉንም* አይታዘዙም።+ 25 ስለዚህ ንዴቱን፣ ቁጣውንና የጦርነቱን መዓትበእስራኤል ላይ አፈሰሰ።+ የጦርነቱም እሳት በዙሪያው ያለውን ሁሉ በላው፤ እሱ ግን አላስተዋለም።+ አቃጠለው፤ እሱ ግን ጨርሶ ልብ አላለም።+ ዘካርያስ 1:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ዘና ብለው በተቀመጡት ብሔራት ላይ እጅግ ተቆጥቻለሁ፤+ ምክንያቱም በመጠኑ ብቻ ተቆጥቼ+ እያለ እነሱ ግን ከልክ ያለፈ እርምጃ ወሰዱ።”’+
15 የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ለሕዝቡና ለማደሪያው ስፍራ ስለራራ መልእክተኞቹን እየላከ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 16 እነሱ ግን የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነድና+ ፈውስ እስከማይገኝላቸው ድረስ በእውነተኛው አምላክ መልእክተኞች ላይ ያላግጡ፣+ ቃሉን ይንቁና+ በነቢያቱ ላይ ያፌዙ+ ነበር።
24 ያዕቆብን ለዘረፋ፣እስራኤልንም ለበዝባዦች አሳልፎ የሰጠ ማን ነው? በእሱ ላይ ኃጢአት በመፈጸም የበደልነው ይሖዋ አይደለም? እነሱ በመንገዱ ለመሄድ አልፈለጉም፤ሕጉንም* አይታዘዙም።+ 25 ስለዚህ ንዴቱን፣ ቁጣውንና የጦርነቱን መዓትበእስራኤል ላይ አፈሰሰ።+ የጦርነቱም እሳት በዙሪያው ያለውን ሁሉ በላው፤ እሱ ግን አላስተዋለም።+ አቃጠለው፤ እሱ ግን ጨርሶ ልብ አላለም።+