የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 28:19, 20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 ይሖዋ በእስራኤል ንጉሥ በአካዝ የተነሳ ይሁዳን አዋረደ፤ ምክንያቱም አካዝ የይሁዳን ሰዎች መረን ለቆ ነበር፤ ይህም ንጉሡ ለይሖዋ የነበረውን ታማኝነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያጓድል አደረገው።

      20 በመጨረሻም የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር+ እሱን ከመርዳት ይልቅ በእሱ ላይ ዘምቶ አስጨነቀው።+

  • ኢሳይያስ 7:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 ይሖዋ፣ ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት+ ጊዜ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ ዘመን በአንተ፣ በሕዝብህና በአባትህ ቤት ላይ ያመጣል፤ የአሦርን ንጉሥ ያመጣልና።+

  • ኢሳይያስ 7:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 “በዚያም ቀን ይሖዋ በወንዙ* አካባቢ ከሚገኘው ቦታ በተከራየው ምላጭ ይኸውም በአሦር ንጉሥ+ አማካኝነት ራሱንና የእግሩን ፀጉር ይላጨዋል፤ ጢሙንም ሙልጭ አድርጎ ያስወግደዋል።

  • ኢሳይያስ 10:28-32
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 28 በአያት+ ላይ መጥቷል፤

      ሚግሮንን አቋርጦ አልፏል፤

      በሚክማሽ+ ጓዙን ያስቀምጣል።

      29 መልካውን* ተሻግረዋል፤

      በጌባ+ ያድራሉ፤

      ራማ ራደች፤ የሳኦል ከተማ ጊብዓ+ ሸሽታለች።+

      30 የጋሊም ሴት ልጅ ሆይ፣ እሪታሽን አቅልጪው!

      ላይሻ ሆይ፣ አዳምጪ!

      ምስኪኗ አናቶት+ ሆይ፣ ጩኺ!

      31 ማድመና ሸሽታለች።

      የጌቢም ነዋሪዎች መሸሸጊያ ፈለጉ።

      32 በዚሁ ቀን በኖብ+ ያርፋል።

      በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ፣

      በኢየሩሳሌም ኮረብታ ላይ እጁን በዛቻ ያወዛውዛል።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ