መዝሙር 107:2, 3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሖዋ የዋጃቸው፣*አዎ፣ ከጠላት እጅ* የዋጃቸው+ ይህን ይበሉ፤ 3 ከምሥራቅና ከምዕራብ፣*ከሰሜንና ከደቡብ፣ከየአገሩ አንድ ላይ የሰበሰባቸው+ ይህን ይናገሩ። ኢሳይያስ 62:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ቅዱስ ሕዝብ፣ ይሖዋ የተቤዣቸው+ ተብለው ይጠራሉ፤አንቺም “እጅግ የምትፈለግ፣” “ያልተተወች ከተማ” ተብለሽ ትጠሪያለሽ።+