20 ከዚያም ንጉሡ ኬልቅያስን፣ የሳፋንን ልጅ አኪቃምን፣+ የሚክያስን ልጅ አብዶንን፣ ጸሐፊውን ሳፋንን እና የንጉሡን አገልጋይ አሳያህን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ 21 “ሄዳችሁ በተገኘው መጽሐፍ ላይ የሰፈረውን ቃል በተመለከተ እኔን እንዲሁም በእስራኤልና በይሁዳ የቀረውን ሕዝብ ወክላችሁ ይሖዋን ጠይቁ፤ አባቶቻችን በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን ነገሮች ሁሉ ስላልፈጸሙና የይሖዋን ቃል ስላልጠበቁ በእኛ ላይ የሚወርደው የይሖዋ ቁጣ ታላቅ ነው።”+