የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 51:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  3 ይሖዋ ጽዮንን ያጽናናታልና።+

      ፍርስራሾቿን ሁሉ ያጽናናል፤+

      ምድረ በዳዋንም እንደ ኤደን፣+

      በረሃማ ሜዳዋንም እንደ ይሖዋ የአትክልት ስፍራ ያደርጋል።+

      በእሷም ውስጥ ሐሴትና ታላቅ ደስታ

      እንዲሁም ምስጋናና ደስ የሚያሰኝ መዝሙር ይገኛሉ።+

  • ኤርምያስ 30:18, 19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

      “እነሆ፣ ከያዕቆብ ድንኳኖች የተማረኩትን እሰበስባለሁ፤+

      ለማደሪያ ድንኳኖቹም እራራለሁ።

      ከተማዋ በጉብታዋ ላይ ዳግም ትገነባለች፤+

      የማይደፈረውም ማማ በተገቢው ቦታ ላይ ይቆማል።

      19 ከእነሱም የምስጋናና የሳቅ ድምፅ ይሰማል።+

      እኔ አበዛቸዋለሁ፤ እነሱም ጥቂት አይሆኑም፤+

      ቁጥራቸው እንዲጨምር* አደርጋለሁ፤

      የተናቁም አይሆኑም።+

  • አሞጽ 9:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ከሕዝቤ ከእስራኤል የተማረኩትን ሰዎች መልሼ እሰበስባለሁ፤+

      እነሱም የወደሙትን ከተሞች መልሰው በመገንባት ይኖሩባቸዋል፤+

      የወይን ተክል ተክለው የወይን ጠጁን ይጠጣሉ፤+

      አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።’+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ