የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 32:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 32 እነሆ፣ ንጉሥ+ ለጽድቅ ይነግሣል፤+

      መኳንንትም ፍትሕ ለማስፈን ይገዛሉ።

  • ኢሳይያስ 60:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 በመዳብ ፋንታ ወርቅ፣

      በብረት ፋንታ ብር፣

      በእንጨት ፋንታ መዳብ፣

      በድንጋዮችም ፋንታ ብረት አመጣለሁ፤

      ሰላምንም የበላይ ተመልካቾችሽ፣

      ጽድቅንም አሠሪዎችሽ አድርጌ እሾማለሁ።+

  • ኤርምያስ 22:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 ‘አንተ ግን ዓይንህና ልብህ ያረፈው አላግባብ በምታገኘው ጥቅም፣

      ንጹሕ ደም በማፍሰስ

      እንዲሁም በማጭበርበርና በቅሚያ ላይ ብቻ ነው።’

  • ኤርምያስ 23:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 “እነሆ፣ ለዳዊት፣ ጻድቅ ቀንበጥ* የማስነሳበት ጊዜ እየደረሰ ነው”+ ይላል ይሖዋ። “ንጉሥም ይገዛል፤+ በማስተዋል ይመላለሳል እንዲሁም በምድሪቱ ላይ ለፍትሕና ለጽድቅ ይቆማል።+

  • ሕዝቅኤል 22:27
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 27 በመካከሏ ያሉት አለቆቿ ያደኑትን እንስሳ እንደሚቦጫጭቁ ተኩላዎች ናቸው፤ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ደም ያፈሳሉ፤ የሰዎችንም ሕይወት* ያጠፋሉ።+

  • ሕዝቅኤል 46:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 አለቃው ሕዝቡን ከይዞታቸው በማፈናቀል የትኛውንም ርስት ሊወስድባቸው አይገባም። ከሕዝቤ መካከል አንዳቸውም ከይዞታቸው እንዳይፈናቀሉ ለወንዶች ልጆቹ ርስት መስጠት ያለበት ከራሱ ይዞታ ላይ ነው።’”

  • ሚክያስ 3:1-3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 እንዲህ አልኩ፦ “እናንተ የያዕቆብ መሪዎችና

      የእስራኤል ቤት ገዢዎች፣ እባካችሁ ስሙ።+

      ትክክል የሆነውን ነገር ማወቅ አይገባችሁም?

       2 ሆኖም እናንተ መልካም የሆነውን ትጠላላችሁ፤+ ክፉ የሆነውን ደግሞ ትወዳላችሁ፤+

      የሕዝቤን ቆዳ ትገፍፋላችሁ፤ ሥጋቸውንም ከአጥንቶቻቸው ትለያላችሁ።+

       3 የሕዝቤንም ሥጋ ትበላላችሁ፤+

      ቆዳቸውንም ትገፍፋላችሁ፤

      አጥንቶቻቸውንም ትሰባብራላችሁ፤+

      በድስት ውስጥ እንዳለ አጥንትና በአፍላል* ውስጥ እንዳለ ሥጋ ትቆራርጧቸዋላችሁ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ