1 ነገሥት 14:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ከዚህ ይልቅ ከአንተ በፊት ከነበሩት ሁሉ የከፋ ድርጊት ፈጸምክ፤ እኔንም ለማስቆጣት ለራስህ ሌላ አምላክና ከብረት የተሠሩ ምስሎችን* ሠራህ፤+ ጀርባህንም ሰጠኸኝ።+ ነህምያ 9:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 “ይሁንና ለመታዘዝ እንቢተኞች በመሆን በአንተ ላይ ዓመፁ፤+ ለሕግህም ጀርባቸውን ሰጡ።* ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩትን ነቢያትህን ገደሉ፤ ከፍተኛ ንቀት የሚንጸባረቅባቸውንም ተግባሮች ፈጸሙ።+ ኢሳይያስ 17:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 አንቺ፣* አዳኝ አምላክሽን ረስተሻልና፤+መሸሸጊያ ዓለትሽንም+ አላስታወስሽም። ያማሩ ተክሎችን ያለማሽውናበመካከሉም የባዕድ* ቡቃያ የተከልሽው ለዚህ ነው። ኤርምያስ 2:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 ለመሆኑ አንዲት ድንግል ጌጣጌጧን፣ሙሽሪትስ ጌጠኛ መቀነቷን* ትረሳለች? የገዛ ሕዝቤ ግን ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ቀናት ረስቶኛል።+ ኤርምያስ 13:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ይህ ዕጣሽ፣ ሰፍሬም የሰጠሁሽ ድርሻሽ ነው” ይላል ይሖዋ፤“ምክንያቱም እኔን ረስተሽኛል፤+ በሐሰትም ትታመኛለሽ።+
9 ከዚህ ይልቅ ከአንተ በፊት ከነበሩት ሁሉ የከፋ ድርጊት ፈጸምክ፤ እኔንም ለማስቆጣት ለራስህ ሌላ አምላክና ከብረት የተሠሩ ምስሎችን* ሠራህ፤+ ጀርባህንም ሰጠኸኝ።+
26 “ይሁንና ለመታዘዝ እንቢተኞች በመሆን በአንተ ላይ ዓመፁ፤+ ለሕግህም ጀርባቸውን ሰጡ።* ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩትን ነቢያትህን ገደሉ፤ ከፍተኛ ንቀት የሚንጸባረቅባቸውንም ተግባሮች ፈጸሙ።+