42 እነሆ፣ ደግፌ የያዝኩት፣
ደስ የምሰኝበትና+ የመረጥኩት+ አገልጋዬ!+
መንፈሴን በእሱ ላይ አድርጌአለሁ፤+
እሱ ለብሔራት ፍትሕን ያመጣል።+
2 አይጮኽም ወይም ድምፁን ከፍ አያደርግም፤
ድምፁንም በጎዳና ላይ አያሰማም።+
3 የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፤
የሚጨስንም የጧፍ ክር አያጠፋም።+
ፍትሕን በታማኝነት ያመጣል።+
4 እሱ ፍትሕን በምድር ላይ እስኪያሰፍን ድረስ አይሰበርም ወይም ብርሃኑ አይደክምም፤+
ደሴቶችም ሕጉን በተስፋ ይጠባበቃሉ።