ዮሐንስ 14:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 የዚህ ዓለም ገዢ+ እየመጣ ስለሆነ ከዚህ በኋላ ከእናንተ ጋር ብዙ አልነጋገርም፤ እሱም በእኔ ላይ ምንም ኃይል የለውም።+ ዮሐንስ 16:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ስለ ፍርድ የተባለው ደግሞ የዚህ ዓለም ገዢ ስለተፈረደበት ነው።+ የሐዋርያት ሥራ 26:17, 18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ወደ እነሱ ከምልክህ ከዚህ ሕዝብና ከአሕዛብ እታደግሃለሁ፤+ 18 የምልክህም የኃጢአት ይቅርታ ያገኙና+ በእኔ ላይ ባላቸው እምነት አማካኝነት በተቀደሱት መካከል ርስት ይቀበሉ ዘንድ ዓይናቸውን እንድትገልጥ+ እንዲሁም ከጨለማ+ ወደ ብርሃን፣+ ከሰይጣን ሥልጣንም+ ወደ አምላክ እንድትመልሳቸው ነው።’ 2 ቆሮንቶስ 4:3, 4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 እንግዲህ የምናውጀው ምሥራች በእርግጥ የተሸፈነ ከሆነ የተሸፈነው ወደ ጥፋት እያመሩ ላሉት ነው፤ 4 የአምላክ አምሳል ስለሆነው ስለ ክርስቶስ+ የሚገልጸውና ክብራማ የሆነው ምሥራች የሚፈነጥቀው ብርሃን በእነሱ ላይ እንዳያበራ+ የዚህ ሥርዓት* አምላክ+ የማያምኑትን ሰዎች አእምሮ አሳውሯል።+ ኤፌሶን 2:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 በተጨማሪም፣ እናንተ በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ምክንያት ሙታን የነበራችሁ ቢሆንም አምላክ ሕያው አድርጓችኋል፤+ 2 በዚያን ጊዜ የዚህን ዓለም ሥርዓት* ተከትላችሁ፣+ የአየሩ ሥልጣን ገዢ+ በሚፈልገው መንገድ ትመላለሱ ነበር፤ ይህም አየር በማይታዘዙት ልጆች ላይ አሁን ተጽዕኖ እያሳደረ ያለ መንፈስ ነው።+ 1 ዮሐንስ 5:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
17 ወደ እነሱ ከምልክህ ከዚህ ሕዝብና ከአሕዛብ እታደግሃለሁ፤+ 18 የምልክህም የኃጢአት ይቅርታ ያገኙና+ በእኔ ላይ ባላቸው እምነት አማካኝነት በተቀደሱት መካከል ርስት ይቀበሉ ዘንድ ዓይናቸውን እንድትገልጥ+ እንዲሁም ከጨለማ+ ወደ ብርሃን፣+ ከሰይጣን ሥልጣንም+ ወደ አምላክ እንድትመልሳቸው ነው።’
3 እንግዲህ የምናውጀው ምሥራች በእርግጥ የተሸፈነ ከሆነ የተሸፈነው ወደ ጥፋት እያመሩ ላሉት ነው፤ 4 የአምላክ አምሳል ስለሆነው ስለ ክርስቶስ+ የሚገልጸውና ክብራማ የሆነው ምሥራች የሚፈነጥቀው ብርሃን በእነሱ ላይ እንዳያበራ+ የዚህ ሥርዓት* አምላክ+ የማያምኑትን ሰዎች አእምሮ አሳውሯል።+
2 በተጨማሪም፣ እናንተ በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ምክንያት ሙታን የነበራችሁ ቢሆንም አምላክ ሕያው አድርጓችኋል፤+ 2 በዚያን ጊዜ የዚህን ዓለም ሥርዓት* ተከትላችሁ፣+ የአየሩ ሥልጣን ገዢ+ በሚፈልገው መንገድ ትመላለሱ ነበር፤ ይህም አየር በማይታዘዙት ልጆች ላይ አሁን ተጽዕኖ እያሳደረ ያለ መንፈስ ነው።+