ኢሳይያስ
3 በዚያ ጊዜ፣ የሚያዩ ሰዎች ዓይኖች አይጨፈኑም፤
የሚሰሙ ሰዎችም ጆሮዎች በትኩረት ያዳምጣሉ።
4 የችኩሎች ልብ እውቀትን ያሰላስላል፤
የሚንተባተብ ምላስም አቀላጥፎና አጥርቶ ይናገራል።+
5 የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ሰው ከእንግዲህ ለጋስ አይባልም፤
ሥርዓት የሌለው ሰውም ትልቅ ሰው አይባልም፤
6 የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ሰው የማይረባ ነገር ይናገራልና፤
ደግሞም በይሖዋ ላይ ክህደት ለመፈጸምና* የውሸት ቃል ለመናገር፣
እንዲሁም የተራበ ሰው የሚበላ ነገር እንዳያገኝና*
የተጠማ ሰው የሚጠጣ ነገር እንዳያገኝ ለማድረግ
ልቡ ክፋትን ያውጠነጥናል።+
7 ሥርዓት የሌለው ሰው የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች መጥፎ ናቸው፤+
ድሃው ትክክል የሆነውን ነገር በሚናገርበት ጊዜም እንኳ
የተጎሳቆለውን ሰው በውሸት ቃል ለማጥፋት
አሳፋሪ ለሆነ ምግባር ድጋፍ ይሰጣል።+
8 ለጋስ ሰው ግን ስለ ልግስና ያስባል፤
ዘወትር የልግስና* ተግባር ለመፈጸም ይተጋል።
9 “እናንተ ደንታ ቢስ ሴቶች፣ ተነሱ፤ ድምፄንም ስሙ!
እናንተ ግድየለሽ ሴቶች ልጆች፣+ የምናገረውን ነገር በትኩረት አዳምጡ!
10 እናንተ ግድየለሾች፣ ከአንድ ዓመት ብዙም ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ትሸበራላችሁ፤
ምክንያቱም የወይን ፍሬ የምትለቅሙበት ጊዜ ሲያልፍ የተሰበሰበ ፍሬ አይኖርም።+
11 እናንተ ደንታ ቢስ ሴቶች፣ ተንቀጥቀጡ!
እናንተ ግድየለሾች፣ ተሸበሩ!
ልብሳችሁን በሙሉ አውልቁ፤
በወገባችሁም ላይ ማቅ ታጠቁ።+
12 ስለ መልካሙ እርሻና ፍሬያማ ስለሆነው ወይን
በሐዘን ደረታችሁን ምቱ።
14 የማይደፈረው ማማ ባዶ ሆኗልና፤
ሁካታ የነበረበት ከተማ ወና ቀርቷል።+
ኦፌልና+ መጠበቂያ ግንቡ ለዘለቄታው ጠፍ ሆነዋል፤
የዱር አህዮች መፈንጫና
የመንጎች መሰማሪያ ሆነዋል፤+
15 ይህም የሚሆነው መንፈስ ከላይ እስኪፈስብን፣+
ምድረ በዳውም የፍራፍሬ እርሻ እስከሚሆን፣
የፍራፍሬ እርሻውም እንደ ጫካ እስከሚቆጠር ድረስ ነው።+
16 ከዚያም በምድረ በዳ ፍትሕ ይሰፍናል፤
በፍራፍሬ እርሻም ጽድቅ ይኖራል።+
18 ሕዝቤ ሰላማዊ በሆነ የመኖሪያ ስፍራ፣
አስተማማኝ በሆነ መኖሪያና ጸጥታ በሰፈነበት የማረፊያ ቦታ ይኖራል።+
19 ሆኖም በረዶው ጫካውን ያወድማል፤
ከተማዋም ሙሉ በሙሉ ትፈራርሳለች።