የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 8
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ኢሳይያስ የመጽሐፉ ይዘት

      • የአሦር ወረራ (1-8)

        • ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ (1-4)

      • አትፍሩ፤ “አምላክ ከእኛ ጋር ነው” (9-17)

      • ኢሳይያስና ልጆቹ ምልክት ሆነው ያገለግላሉ (18)

      • አጋንንትን ከመጠየቅ ይልቅ ሕጉን ተመልከቱ (19-22)

ኢሳይያስ 8:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ሟች በሆነ ሰው ብዕር።”

  • *

    “ወደ ምርኮው ፈጥኖ መሄድ፣ ወደ ብዝበዛው ፈጥኖ መምጣት” የሚል ትርጉም ሊኖረው ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 30:8

ኢሳይያስ 8:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ይመሥክሩልኝ፤ ቃላቸውን ይስጡልኝ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 16:10

ኢሳይያስ 8:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    የኢሳይያስን ሚስት ታመለክታለች።

  • *

    ቃል በቃል “ወደ ነቢዪቱ ቀረብኩ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 8:18

ኢሳይያስ 8:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 15:29፤ 16:8, 9፤ 17:6፤ ኢሳ 7:16፤ 17:1

ኢሳይያስ 8:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ሺሎአ የውኃ ቦይ ነበር።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:16፤ ኤር 17:13
  • +ኢሳ 7:1

ኢሳይያስ 8:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ኤፍራጥስን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 17:5፤ 18:9

ኢሳይያስ 8:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ኢሳ 7:14ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 28:19, 20፤ ኢሳ 7:17, 20፤ 10:28-32
  • +ኢሳ 7:14፤ ማቴ 1:23

ኢሳይያስ 8:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ታጠቁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 32:21

ኢሳይያስ 8:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “አምላክ ከእኛ ጋር ነው” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል ኢማኑኤል የሚለው ነው። ኢሳ 7:14ንና 8:8ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 20:1፤ መዝ 44:3

ኢሳይያስ 8:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 10:3፤ 22:32
  • +መክ 12:13፤ ማቴ 10:28

ኢሳይያስ 8:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 21:42, 44፤ ሉቃስ 20:17, 18፤ ሮም 9:31-33፤ 1ቆሮ 1:23፤ 1ጴጥ 2:7, 8

ኢሳይያስ 8:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የምሥክርነት ቃል።”

  • *

    ወይም “መመሪያውን፤ ትምህርቱን።”

ኢሳይያስ 8:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በጉጉት እጠብቃለሁ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:16, 17፤ ሚክ 3:4
  • +መዝ 33:20

ኢሳይያስ 8:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 2:13
  • +ኢሳ 7:14, 16፤ 8:3, 4

ኢሳይያስ 8:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 20:6፤ ዘዳ 18:10, 11፤ መዝ 146:4፤ መክ 9:5, 10

ኢሳይያስ 8:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የምሥክርነት ቃሉን።”

  • *

    ቃል በቃል “አይነጋላቸውም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 4:19

ኢሳይያስ 8:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 28:15, 48

ተዛማጅ ሐሳብ

ኢሳ. 8:1ኢሳ 30:8
ኢሳ. 8:22ነገ 16:10
ኢሳ. 8:3ኢሳ 8:18
ኢሳ. 8:42ነገ 15:29፤ 16:8, 9፤ 17:6፤ ኢሳ 7:16፤ 17:1
ኢሳ. 8:62ነገ 17:16፤ ኤር 17:13
ኢሳ. 8:6ኢሳ 7:1
ኢሳ. 8:72ነገ 17:5፤ 18:9
ኢሳ. 8:82ዜና 28:19, 20፤ ኢሳ 7:17, 20፤ 10:28-32
ኢሳ. 8:8ኢሳ 7:14፤ ማቴ 1:23
ኢሳ. 8:92ዜና 32:21
ኢሳ. 8:10ዘዳ 20:1፤ መዝ 44:3
ኢሳ. 8:13ዘሌ 10:3፤ 22:32
ኢሳ. 8:13መክ 12:13፤ ማቴ 10:28
ኢሳ. 8:14ማቴ 21:42, 44፤ ሉቃስ 20:17, 18፤ ሮም 9:31-33፤ 1ቆሮ 1:23፤ 1ጴጥ 2:7, 8
ኢሳ. 8:17ዘዳ 31:16, 17፤ ሚክ 3:4
ኢሳ. 8:17መዝ 33:20
ኢሳ. 8:18ዕብ 2:13
ኢሳ. 8:18ኢሳ 7:14, 16፤ 8:3, 4
ኢሳ. 8:19ዘሌ 20:6፤ ዘዳ 18:10, 11፤ መዝ 146:4፤ መክ 9:5, 10
ኢሳ. 8:20ምሳሌ 4:19
ኢሳ. 8:21ዘዳ 28:15, 48
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ኢሳይያስ 8:1-22

ኢሳይያስ

8 ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “አንድ ትልቅ ጽላት+ ወስደህ በብዕር* ‘ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ’* ብለህ ጻፍ። 2 ታማኝ ምሥክሮች የሆኑት ካህኑ ኦርዮና+ የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ደግሞ የጽሑፍ ማረጋገጫ ይስጡኝ።”*

3 እኔም ከነቢዪቱ* ጋር ተገናኘሁ፤* እሷም ፀነሰች፤ በኋላም ወንድ ልጅ ወለደች።+ ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ስሙን ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ ብለህ ጥራው፤ 4 ልጁ ‘አባዬ!’ እና ‘እማዬ!’ ብሎ መጥራት ከመቻሉ በፊት የደማስቆ ሀብትና የሰማርያ ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወሰዳል።”+

5 ይሖዋ በድጋሚ እንዲህ አለኝ፦

 6 “ይህ ሕዝብ ቀስ ብለው የሚወርዱትን የሺሎአ* ውኃዎች ንቆ+

በረጺንና በረማልያህ+ ልጅ ሐሴት ስላደረገ

 7 እነሆ፣ ይሖዋ ብርቱ የሆኑትንና ከፍተኛ መጠን ያላቸውን የወንዙን* ውኃዎች ይኸውም

የአሦርን ንጉሥና+ ክብሩን ሁሉ

በእነሱ ላይ ያመጣባቸዋል።

እሱም የውኃ መውረጃዎቹን ሁሉ ሞልቶ ይፈስሳል፤

ዳርቻዎቹንም ሁሉ ያጥለቀልቃል፤

 8 ይሁዳንም ጠራርጎ ይሄዳል።

አካባቢውን እያጥለቀለቀ በማለፍ እስከ አንገት ይደርሳል፤+

አማኑኤል*+ ሆይ፣ የተዘረጉት ክንፎቹ

ምድርህን ከዳር እስከ ዳር ይሸፍናሉ!”

 9 እናንተ ሕዝቦች፣ ጉዳት አድርሱባቸው፤ ሆኖም ድምጥማጣችሁ ይጠፋል።

ራቅ ባሉ የምድር ክፍሎች የምትኖሩ ሁሉ አዳምጡ!

ለውጊያ ተዘጋጁ፤* ነገር ግን ድምጥማጣችሁ ይጠፋል!+

ለውጊያ ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ድምጥማጣችሁ ይጠፋል!

10 ዕቅድ አውጡ፤ ይሁንና ይጨናገፋል!

የፈለጋችሁትን ተናገሩ፤ ሆኖም አይሳካም፤

አምላክ ከእኛ ጋር ነውና!*+

11 ይሖዋ ብርቱ እጁን በእኔ ላይ አድርጎ የዚህን ሕዝብ መንገድ እንዳልከተል ለማስጠንቀቅ እንዲህ አለኝ፦

12 “ይህ ሕዝብ ‘ሴራ እንጠንስስ!’ ሲል እናንተ ‘በሴራው ተባበሩ!’ አትበሉ፤

እነሱ የሚያስፈራቸውን ነገር አትፍሩ፤

አትንቀጥቀጡለትም።

13 ቅዱስ አድርጋችሁ ልትመለከቱ የሚገባው የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ነው፤+

ልትፈሩ የሚገባው እሱን ነው፤

እንዲሁም ልትንቀጠቀጡ የሚገባው ለእሱ ነው።”+

14 እሱ እንደ መቅደስ ይሆናል፤

ለሁለቱ የእስራኤል ቤቶች ግን

እንደሚያሰናክል ድንጋይና

እንደሚያደናቅፍ ዓለት፣+

ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎችም

እንደ ወጥመድና እንደ አሽክላ ይሆንባቸዋል።

15 ከእነሱ መካከል ብዙዎቹ ይደናቀፋሉ፣ ይወድቃሉ፣ ይሰበራሉ፤

ወጥመድ ውስጥ ገብተው ይያዛሉ።

16 በጽሑፍ የሰፈረውን ማረጋገጫ* ጠቅልለው፤

ሕጉን* በደቀ መዛሙርቴ መካከል አሽገው!

17 እኔም ፊቱን ከያዕቆብ ቤት የሰወረውን+ ይሖዋን እጠባበቃለሁ፤*+ በእሱም ተስፋ አደርጋለሁ።

18 እነሆ፣ እኔና ይሖዋ የሰጠኝ ልጆች+ በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከይሖዋ ለእስራኤል እንደተሰጡ ምልክቶችና+ ተአምራት ነን።

19 እነሱም “የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሹኩትን መናፍስት ጠሪዎች ወይም ጠንቋዮች ጠይቁ” ቢሏችሁ፣ አንድ ሕዝብ መጠየቅ ያለበት የራሱን አምላክ አይደለም? ስለ ሕያዋንስ ሙታንን መጠየቁ ተገቢ ነው?+ 20 ከዚህ ይልቅ ሕጉንና የማረጋገጫ ሰነዱን* መመርመር ይገባቸዋል!

ከዚህ ቃል ጋር የሚስማማ ነገር ሳይናገሩ ሲቀሩ ብርሃን አይበራላቸውም።*+ 21 እያንዳንዱም ተጎሳቁሎና ተርቦ በምድሪቱ ላይ ይንከራተታል፤+ ከመራቡና ከመበሳጨቱ የተነሳ ወደ ላይ እያየ ንጉሡንና አምላኩን ይረግማል። 22 ከዚያም ወደ ምድር ይመለከታል፤ የሚያየውም ነገር ጭንቀትና ጨለማ፣ ግራ የሚያጋባ ሁኔታ፣ አስቸጋሪ ወቅትና ብርሃን የሌለበት ፅልማሞት ብቻ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ