አሞጽ
1 በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያና+ በእስራኤል ንጉሥ በዮአስ+ ልጅ በኢዮርብዓም+ ዘመን፣ የመሬት መንቀጥቀጡ+ ከመከሰቱ ከሁለት ዓመት በፊት በተቆአ+ ከነበሩት በግ አርቢዎች መካከል አንዱ ለሆነው ለአሞጽ* ስለ እስራኤል በራእይ የተገለጠለት ቃል። 2 እሱ እንዲህ ብሏል፦
“ይሖዋ ከጽዮን እንደ አንበሳ ያገሳል፤
ከኢየሩሳሌምም ድምፁን በኃይል ያሰማል።
የእረኞቹ ማሰማሪያዎች ያለቅሳሉ፤
የቀርሜሎስም አናት ይደርቃል።”+
5 የደማስቆን በሮች መቀርቀሪያ እሰብራለሁ፤+
የቢቃትአዌን ነዋሪዎችን አጠፋለሁ፤
በቤትኤደን ተቀምጦ የሚገዛውን* አስወግዳለሁ፤
የሶርያ ሰዎችም ወደ ቂር በግዞት ይሄዳሉ”+ ይላል ይሖዋ።’
7 በመሆኑም በጋዛ ቅጥር ላይ እሳት እሰዳለሁ፤+
የማይደፈሩ ማማዎቿንም ይበላል።
8 የአሽዶድን ነዋሪዎች አጠፋለሁ፤+
በአስቀሎን ተቀምጦ የሚገዛውንም* አስወግዳለሁ፤+
እጄን በኤቅሮን ላይ እዘረጋለሁ፤+
የተረፉት ፍልስጤማውያንም ይጠፋሉ”+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።’
9 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘ስለ ሦስቱ የጢሮስ ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤
ምክንያቱም ሕዝቡን ሁሉ ማርከው ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል፤
ደግሞም የወንድማማቾችን ቃል ኪዳን አላስታወሱም።+
10 በመሆኑም በጢሮስ ቅጥር ላይ እሳት እሰዳለሁ፤
የማይደፈሩ ማማዎቿንም ይበላል።’+
11 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘ስለ ሦስቱ የኤዶም ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤
ምክንያቱም የገዛ ወንድሙን በሰይፍ አሳዷል፤+
ምሕረት ለማሳየትም እንቢተኛ ሆኗል፤
በቁጣው ያላንዳች ፋታ ይዘነጣጥላቸዋል፤
አሁንም ቢሆን በእነሱ ላይ ቁጣው አልበረደም።+
13 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘“ስለ ሦስቱ የአሞናውያን ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤
ምክንያቱም ግዛታቸውን ለማስፋት ሲሉ የጊልያድን ነፍሰ ጡር ሴቶች ሆድ ቀደዋል።+
15 ንጉሣቸውም ከመኳንንቱ ጋር በግዞት ይወሰዳል”+ ይላል ይሖዋ።’
2 በመሆኑም በሞዓብ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤
የቀሪዮትንም+ የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል፤
ሞዓብ በትርምስ፣
በቀረርቶና በቀንደ መለከት ድምፅ መካከል ይሞታል።+
4 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘ስለ ሦስቱ የይሁዳ ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤
ምክንያቱም የይሖዋን ሕግ* ንቀዋል፤
ሥርዓቱንም አልጠበቁም፤+
ይልቁንም አባቶቻቸው በተከተሉት በዚያው ውሸት ስተዋል።+
5 በመሆኑም በይሁዳ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤
የኢየሩሳሌምንም የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል።’+
አባትና ልጅ ከአንዲት ሴት ጋር ግንኙነት በመፈጸም
ቅዱስ ስሜን ያረክሳሉ።
9 ‘ይሁንና ቁመቱ እንደ አርዘ ሊባኖስ፣ ጥንካሬውም እንደ ባሉጥ ዛፍ የሆነውን አሞራዊ
በፊታቸው ያጠፋሁት እኔ ነኝ፤+
ከላይ ያለውን ፍሬውንም ሆነ ከታች ያሉትን ሥሮቹን አጠፋሁ።+
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ይህን አላደረግኩም?’ ይላል ይሖዋ።
13 ስለዚህ በታጨደ እህል የተሞላ ጋሪ ከሥሩ ያለውን እንደሚያደቅ፣
ባላችሁበት ስፍራ አደቃችኋለሁ።
3 “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ይሖዋ ስለ እናንተ ይኸውም ከግብፅ ምድር ስላወጣሁት ስለ መላው ብሔር የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፦
2 ‘በምድር ላይ ካሉ ብሔራት ሁሉ እኔ የማውቀው እናንተን ብቻ ነው።+
ስለዚህ ለፈጸማችሁት በደል ሁሉ ተጠያቂ አደርጋችኋለሁ።+
3 ሁለት ሰዎች ለመገናኘት ሳይስማሙ* አብረው ይጓዛሉ?
4 አንበሳ አድኖ ሳይዝ በጫካ ውስጥ ያገሳል?
ደቦል አንበሳስ ምንም ነገር ሳይዝ በዋሻው ውስጥ ሆኖ ያጉረመርማል?
5 ወጥመድ ሳይዘጋጅ* ወፍ መሬት ላይ ይጠመዳል?
ወጥመድስ ምንም ነገር ሳይዝ ይፈነጠራል?
6 በከተማ ውስጥ ቀንደ መለከት ቢነፋ ሕዝቡ አይሸበርም?
በከተማው ውስጥ ጥፋት ቢከሰት ይህን ያደረገው ይሖዋ አይደለም?
8 አንበሳ አገሳ!+ የማይፈራ ማን ነው?
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ተናገረ! ትንቢት የማይናገር ማን ነው?’+
9 ‘በአሽዶድ በሚገኙ የማይደፈሩ ማማዎች
ደግሞም በግብፅ ምድር በሚገኙ የማይደፈሩ ማማዎች ላይ አውጁት።
10 በማይደፈሩ ማማዎቻቸው ውስጥ ዓመፅንና ጥፋትን የሚያከማቹ ሰዎች
ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ አያውቁምና” ይላል ይሖዋ።’
12 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት ቅልጥም ወይም የጆሮ ቁራጭ ነጥቆ እንደሚወስድ ሁሉ
በሰማርያ ባማረ አልጋና ምርጥ በሆነ ድንክ አልጋ* የሚቀመጡ
የእስራኤል ሰዎችም ተነጥቀው ይወሰዳሉ።’+
13 ‘ስሙ፤ የያዕቆብንም ቤት አስጠንቅቁ’* ይላል የሠራዊት አምላክ የሆነው ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
14 ‘እስራኤልን ለፈጸመው የዓመፅ ድርጊት* ሁሉ ተጠያቂ በማደርገው ቀን+
የቤቴልንም መሠዊያዎች ተጠያቂ አደርጋለሁና፤+
የመሠዊያው ቀንዶች ተቆርጠው ወደ ምድር ይወድቃሉ።+
15 የክረምቱን ቤትና የበጋውን ቤት አፈርሳለሁ።’
4 “እናንተ በሰማርያ ተራራ ላይ ያላችሁ፣+
ችግረኛ በሆኑ ሰዎች ላይ ግፍ የምትፈጽሙና+ ድሆችን የምትጨቁኑ ሴቶች፣
ባሎቻችሁንም* ‘የምንጠጣው ነገር አምጡልን!’
የምትሉ የባሳን ላሞች ሆይ፣ ይህን ቃል ስሙ።
2 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በቅድስናው ምሏል፤
‘“እነሆ፣ እናንተን በሜንጦ፣
ከእናንተ የቀሩትንም በመንጠቆ የሚያነሳበት ቀን እየመጣባችሁ ነው።
3 እያንዳንዳችሁ ከፊታችሁ በምታገኟቸው፣ በቅጥሩ ላይ ባሉት ክፍተቶች በኩል ትወጣላችሁ፤
ወደ ሃርሞንም ትጣላላችሁ” ይላል ይሖዋ።’
5 እርሾ ያለበትን ዳቦ የሚቃጠል የምስጋና መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤+
በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትንም መባ በአዋጅ አስነግሩ!
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ማድረግ የምትወዱት ይህን ነውና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
7 ‘በተጨማሪም መከር ከመድረሱ ከሦስት ወር በፊት ዝናብ ከለከልኳችሁ፤+
በአንዱ ከተማ ዝናብ እንዲዘንብ ሳደርግ በሌላው ከተማ ግን እንዳይዘንብ አደረግኩ።
አንዱ እርሻ ዝናብ ያገኛል፤
ዝናብ ያላገኘው ሌላው እርሻ ግን ይደርቃል።
8 በሁለት ወይም በሦስት ከተሞች የሚኖሩ ሰዎች ውኃ ለመጠጣት ወደ አንዲት ከተማ እያዘገሙ ሄዱ፤+
ይሁንና ጥማቸውን ማርካት አልቻሉም፤
እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’+ ይላል ይሖዋ።
9 ‘በሚያቃጥል ሙቀትና በዋግ መታኋችሁ።+
የአትክልት ስፍራዎቻችሁንና የወይን እርሻዎቻችሁን አበዛችሁ፤
ይሁንና የበለስ ዛፎቻችሁንና የወይራ ዛፎቻችሁን አንበጣ ይበላቸዋል፤+
ያም ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’+ ይላል ይሖዋ።
10 ‘በግብፅ ላይ የደረሰውን ዓይነት ቸነፈር ሰደድኩባችሁ።+
ወጣቶቻችሁን በሰይፍ ገደልኩ፤+ ፈረሶቻችሁንም ማረክሁ።+
የሰፈሮቻችሁ ግማት ወደ አፍንጫችሁ እንዲገባ አደረግኩ፤+
እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’ ይላል ይሖዋ።
11 ‘ሰዶምንና ገሞራን እንደገለበጥኳቸው ሁሉ
ምድራችሁን ገለበጥኩ።+
እናንተም ከእሳት እንደተነጠቀ ጉማጅ ነበራችሁ፤
ያም ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’+ ይላል ይሖዋ።
12 ስለዚህ እስራኤል ሆይ፣ እንዲሁ አደርግብሃለሁ።
እስራኤል ሆይ፣ ይህን ነገር ስለማደርግብህ
አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ።
13 እነሆ፣ ተራሮችን የሠራው፣+ ነፋስን የፈጠረው እሱ ነው፤+
ሐሳቡ ምን እንደሆነ ለሰው ይነግረዋል፤
የንጋት ብርሃንን ያጨልማል፤+
በምድር ላይ ያሉ ከፍ ያሉ ስፍራዎችን ይረግጣል፤+
ስሙ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ነው።”
5 “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእናንተ ላይ እንደ ሙሾ* አድርጌ የምናገረውን ይህን ቃል ስሙ፦
2 ‘ድንግሊቱ እስራኤል ወድቃለች፤
ዳግመኛም አትነሳም።
በገዛ ምድሯ ተጥላለች፤
የሚያነሳትም የለም።’
3 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦
‘አንድ ሺህ ሰዎች ይዛ የምትዘምት ከተማ መቶ ሰዎች ብቻ ይቀሯታል፤
መቶ ሰዎች ይዛ የምትዘምት ከተማም አሥር ሰዎች ብቻ ይቀሯታል። ይህ በእስራኤል ቤት ላይ ይደርሳል።’+
4 “ይሖዋ ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላልና፦
‘እኔን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።+
8 የኪማ ኅብረ ከዋክብትንና* የከሲል ኅብረ ከዋክብትን* የሠራው፣+
ድቅድቅ ጨለማን ወደ ንጋት ብርሃን የሚለውጠው፣
ቀኑንም እንደ ሌሊት ጨለማ የሚያደርገው፣+
ወደ ምድር ያፈሰው ዘንድ
የባሕርን ውኃ ወደ እሱ የሚጠራው፣+
ስሙ ይሖዋ ነው።
9 የተመሸጉትን ቦታዎች በማውደም፣
ብርቱ በሆነው ላይ ድንገተኛ ጥፋት ያመጣል።
10 እነሱ በከተማዋ በር ላይ ሆነው የሚወቅሱትን ይጠላሉ፤
እውነት የሚናገሩትንም ይጸየፋሉ።+
11 ድሃው ለእርሻ ቦታው ኪራይ* እንዲከፍል ስለምታደርጉ፣
እህሉንም በግብር መልክ ስለምትወስዱ፣+
በተጠረበ ድንጋይ በሠራችሁት ቤት ውስጥ አትኖሩም፤+
ደግሞም ከተከላችኋቸው ምርጥ የወይን ተክሎች የሚገኘውን የወይን ጠጅ አትጠጡም።+
12 ዓመፃችሁ* ምን ያህል እንደበዛና
ኃጢአታችሁ ምንኛ ታላቅ እንደሆነ አውቃለሁና፤
ጻድቁን ትጨቁናላችሁ፤
ጉቦ* ትቀበላላችሁ፤
በከተማዋም በር ላይ የድሆችን መብት ትነፍጋላችሁ።+
13 ስለሆነም ጥልቅ ማስተዋል ያላቸው ሰዎች በዚያን ጊዜ ዝም ይላሉ፤
የመከራ ጊዜ ይሆናልና።+
የሠራዊት አምላክ ይሖዋም
እንደተናገራችሁት ከእናንተ ጋር ይሆናል።+
የሠራዊት አምላክ ይሖዋ
ከዮሴፍ ለቀሩት ሰዎች ሞገሱን ያሳያቸው ይሆናል።’+
16 “ስለዚህ ይሖዋ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
‘በየአደባባዩ ዋይታ ይሆናል፤
በየመንገዱም ሰዎች “ወዮ! ወዮ!” ይላሉ።
ገበሬዎችን ለለቅሶ፣
አስለቃሾችንም ለዋይታ ይጠራሉ።’
17 ‘በየወይን እርሻውም ዋይታ ይኖራል፤+
እኔ በመካከልህ አልፋለሁና’ ይላል ይሖዋ።
18 ‘የይሖዋን ቀን ለሚናፍቁ ወዮላቸው!+
የይሖዋ ቀን ለእናንተ ምን ያመጣ ይሆን?+
ያ ቀን ጨለማ እንጂ ብርሃን አይሆንም።+
19 ይህም ሰው ከአንበሳ ሲሸሽ ድብ እንደሚያጋጥመው፣
ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳው ላይ ሲያስደግፍም እባብ እንደሚነድፈው ዓይነት ይሆናል።
20 የይሖዋ ቀን ብርሃን የሌለበት ድቅድቅ ጨለማ ይሆን የለም?
ደግሞስ የብርሃን ጸዳል የሌለበት ጨለማ ይሆን የለም?
21 በዓሎቻችሁን እጠላለሁ፤ ደግሞም እንቃለሁ፤+
የተቀደሱ ጉባኤዎቻችሁ መዓዛም ደስ አያሰኘኝም።
22 ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና የስጦታ መባዎች ብታቀርቡልኝ እንኳ
እነዚህ መባዎች አያስደስቱኝም፤+
ለኅብረት መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡ እንስሳትም በሞገስ ዓይን አልመለከትም።+
23 የተደበላለቁ መዝሙሮችህን ከእኔ አርቅ፤
በባለ አውታር መሣሪያዎች የምትጫወተውንም ዜማ መስማት አልፈልግም።+
24 ፍትሕ እንደ ውኃ፣+
ጽድቅም ያለማቋረጥ እንደሚወርድ ጅረት ይፍሰስ።
25 የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለ40 ዓመት በምድረ በዳ በቆያችሁበት ጊዜ
መሥዋዕትና የስጦታ መባ አቅርባችሁልኝ ነበር?+
26 አሁንም ለራሳችሁ የሠራችኋቸውን፣ ንጉሣችሁ የሆነውን የሳኩትን እንዲሁም የኪዋንን* ምስሎች፣
ይኸውም የአምላካችሁን ኮከብ ተሸክማችሁ ትሄዳላችሁ።
27 እኔም ከደማስቆ ወዲያ ርቃችሁ በግዞት እንድትወሰዱ አደርጋለሁ’+ ይላል ስሙ ይሖዋ የሆነው የሠራዊት አምላክ።”+
6 “በጽዮን በራሳቸው ተማምነው* የሚኖሩ፣
በሰማርያም ተራራ ያለስጋት የተቀመጡ ወዮላቸው!+
እነሱ ከብሔራት ሁሉ መካከል ዋነኛ በሆነው ብሔር ውስጥ የጎላ ስፍራ ያላቸው ናቸው፤
የእስራኤል ቤትም ወደ እነሱ ይመጣል።
2 ወደ ካልኔ ተሻግራችሁ ተመልከቱ።
ከዚያም ተነስታችሁ ወደ ታላቋ ሃማት+ ሂዱ፤
የፍልስጤማውያን ከተማ ወደሆነችውም ወደ ጌት ውረዱ።
እነሱ ከእነዚህ መንግሥታት* ይሻላሉ?
የምድራቸውስ ስፋት ከእናንተ ይበልጣል?
4 የመንጋውን ጠቦቶች እንዲሁም የሰቡ ጥጃዎችን* እየበሉ+
ከዝሆን ጥርስ በተሠራ አልጋ ላይ ይተኛሉ፤+ በድንክ አልጋም ላይ ይንጋለላሉ፤+
5 በገና* እየተጫወቱ የመጣላቸውን ዘፈን ያቀናብራሉ፤+
እንደ ዳዊትም የሙዚቃ መሣሪያዎች+ ይፈለስፋሉ፤
6 በትላልቅ ጽዋዎች የወይን ጠጅ ሞልተው ይጠጣሉ፤+
ምርጥ የሆኑ ዘይቶችም ይቀባሉ።
በዮሴፍ ላይ ስለደረሰው መቅሰፍት ግን ግድ የላቸውም።+
7 ስለዚህ እነሱ በግዞት ከሚወሰዱት መካከል የመጀመሪያዎቹ ይሆናሉ፤+
ተንጋለው በመዝናናት የሚያሳልፉት ጊዜም ያበቃል።
8 ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በራሱ* ምሏል’+ ይላል የሠራዊት አምላክ ይሖዋ፤
‘“የያዕቆብን ኩራት እጸየፋለሁ፤+
የማይደፈሩ ማማዎቹን እጠላለሁ፤+
ከተማዋንና በውስጧ ያለውን ነገር ሁሉ አሳልፌ እሰጣለሁ።+
9 “‘“በአንድ ቤት ውስጥ አሥር ሰዎች ቢቀሩ እነሱም ይሞታሉ። 10 እነሱን አንድ በአንድ አውጥቶ ለማቃጠል አንድ ዘመድ* ይመጣል። አጥንቶቻቸውን ከቤት ውስጥ ያወጣል፤ ከዚያም በቤቱ ውስጠኛ ክፍል ላለ ሰው ‘ከአንተ ጋር የቀሩ ሌሎች ሰዎች አሉ?’ ይለዋል። ሰውየውም ‘ማንም የለም!’ ይላል። ከዚያም ‘ዝም በል! ይህ የይሖዋ ስም የሚጠራበት ጊዜ አይደለም’ ይላል።”
12 ፈረሶች በቋጥኝ ላይ ይሮጣሉ?
ሰውስ እዚያ ላይ በከብት ያርሳል?
14 ስለዚህ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእናንተ ላይ አንድ ብሔር አመጣለሁ’+ ይላል የሠራዊት አምላክ ይሖዋ፤
7 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይህን አሳየኝ፦ እነሆ በኋለኛው ወቅት የተዘራው እህል* መብቀል በጀመረበት ጊዜ እሱ የአንበጣ መንጋ ሰደደ። ይህም የንጉሡ ድርሻ የሆነው ሣር ታጭዶ ሲያበቃ በኋለኛው ወቅት የበቀለ እህል ነበር። 2 የአንበጣው መንጋ በምድሪቱ ላይ የበቀለውን ተክል ሁሉ በልቶ በጨረሰ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ይቅር በል!+ ያዕቆብ ይህን እንዴት ሊቋቋም ይችላል? እሱ አቅመ ቢስ ነውና!”+
3 በመሆኑም ይሖዋ ጉዳዩን በድጋሚ አጤነ።*+ ይሖዋም “ይህ አይፈጸምም” አለ።
4 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይህን አሳየኝ፦ እነሆ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በእሳት እንደሚቀጣ ተናገረ። እሳቱም የተንጣለለውን ጥልቅ ውኃ በላ፤ ደግሞም የተወሰነውን የምድሪቱን ክፍል በላ። 5 በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ይህ ነገር እንዲደርስ አታድርግ።+ ያዕቆብ ይህን እንዴት ሊቋቋም ይችላል? እሱ አቅመ ቢስ ነውና!”+
6 በመሆኑም ይሖዋ ጉዳዩን በድጋሚ አጤነ።*+ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋም “ይህም ቢሆን አይፈጸምም” አለ።
7 እሱም ይህን አሳየኝ፦ እነሆ ይሖዋ በቱምቢ በተሠራ ቅጥር ላይ ቆሞ ነበር፤ በእጁም ቱምቢ ይዞ ነበር። 8 ከዚያም ይሖዋ “አሞጽ፣ ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም “ቱምቢ” አልኩ። ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “እነሆ፣ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ቱምቢ እዘረጋለሁ። ከእንግዲህ ወዲህ ይቅርታ አላደርግላቸውም።+ 9 የይስሐቅ ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች+ ይወድማሉ፤ የእስራኤልም መቅደሶች ይፈራርሳሉ፤+ ደግሞም በኢዮርብዓም* ቤት ላይ ሰይፍ ይዤ እመጣለሁ።”+
10 የቤቴል ካህን የሆነው አሜስያስ+ ለእስራኤል ንጉሥ ለኢዮርብዓም+ ይህን መልእክት ላከ፦ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል በአንተ ላይ እያሴረ ነው።+ ምድሪቱ የእሱን ቃል ሁሉ መታገሥ አትችልም።+ 11 አሞጽ እንዲህ ይላልና፦ ‘ኢዮርብዓም በሰይፍ ይገደላል፤ እስራኤልም ያላንዳች ጥርጥር ከምድሩ ተፈናቅሎ በግዞት ይወሰዳል።’”+
12 ከዚያም አሜስያስ አሞጽን እንዲህ አለው፦ “አንተ ባለ ራእይ፣ ሂድ፤ ወደ ይሁዳም ምድር ሽሽ፤ ቀለብህን ከዚያ አግኝ፤ በዚያም ትንቢት ተናገር።+ 13 ከእንግዲህ ወዲያ ግን በቤቴል ትንቢት አትናገር፤+ ቤቴል የንጉሥ መቅደስና+ የመንግሥት መኖሪያ ናትና።”
14 በዚህ ጊዜ አሞጽ ለአሜስያስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤ ከዚህ ይልቅ እረኛና+ የሾላ ዛፎች የምንከባከብ* ሰው ነኝ። 15 ይሖዋ ግን ከመንጋ ጠባቂነት ወሰደኝ፤ ይሖዋም ‘ሂድና ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር’ አለኝ።+ 16 እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስማ፦ ‘አንተ “በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፤+ በይስሐቅም ቤት ላይ አትስበክ”+ እያልክ ነው። 17 በመሆኑም ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሚስትህ በከተማዋ ውስጥ ዝሙት አዳሪ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ደግሞ በሰይፍ ይወድቃሉ። ምድርህም በገመድ እየተለካ ይከፋፈላል፤ አንተ ራስህም በረከሰ ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ያላንዳች ጥርጥር ከምድሩ ተፈናቅሎ በግዞት ይወሰዳል።”’”+
8 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይህን አሳየኝ፦ እነሆ፣ የበጋ ፍሬ* የያዘ ቅርጫት ነበር። 2 ከዚያም “አሞጽ፣ ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም “የበጋ ፍሬ የያዘ ቅርጫት” ብዬ መለስኩ። ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “የሕዝቤ የእስራኤል ፍጻሜ ደርሷል። ከእንግዲህ ወዲህ ይቅር አልላቸውም።+ 3 ‘በዚያን ቀን የቤተ መቅደሱ መዝሙሮች ወደ ዋይታ ይቀየራሉ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘በየቦታው የተጣሉ ብዙ አስከሬኖች ይኖራሉ፤+ ዝምታ ይስፈን!’
4 እናንተ ድሆችን የምትረጋግጡ፣
በምድሪቱ ላይ ያሉትንም የዋሆች የምታጠፉ ይህን ስሙ፤+
5 እንዲህም ትላላችሁ፦ ‘እህላችንን መሸጥ እንድንችል የወር መባቻው የሚያልፈው መቼ ነው?+
አዝመራችንንስ መሸጥ እንድንችል ሰንበት+ የሚያልፈው መቼ ነው?
ያን ጊዜ በሐሰተኛ ሚዛን ለማጭበርበር
የኢፍ* መስፈሪያውን ማሳነስ፣
6 ደግሞም ችግረኛውን በብር፣
ድሃውንም በጥንድ ጫማ ዋጋ እንገዛለን፤+
መናኛውንም እህል መሸጥ እንችላለን።’
ምድሪቱ በሙሉ እንደ አባይ ወደ ላይ አትነሳም?
በግብፅ እንዳለውም የአባይ ወንዝ ወደ ላይ ከወጣች በኋላ ተመልሳ ወደ ታች አትወርድም?’+
ወገብን ሁሉ ማቅ አስታጥቃለሁ፤ ራስንም ሁሉ እመልጣለሁ፤
ለአንድያ ልጅ እንደሚለቀስ ያለቅሳሉ፤
ፍጻሜውም እንደ መራራ ቀን ይሆናል።’
11 ‘እነሆ፣ በምድሪቱ ላይ ረሃብ የምሰድበት ጊዜ ይመጣል’
ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤
‘ረሃቡ የይሖዋን ቃል የመስማት ረሃብ እንጂ
ምግብን የመራብ ወይም ውኃን የመጠማት አይደለም።+
12 እነሱ ከባሕር ወደ ባሕር፣
ከሰሜንም ወደ ምሥራቅ* ይባዝናሉ።
የይሖዋን ቃል ፍለጋ በየቦታው ይንከራተታሉ፤ ሆኖም አያገኙትም።
13 በዚያ ቀን፣ ውብ የሆኑት ደናግልና
ወጣት ወንዶች ከውኃ ጥም የተነሳ ራሳቸውን ይስታሉ፤
14 በሰማርያ በደል+ የሚምሉ
ደግሞም “ዳን ሆይ፣ ሕያው በሆነው በአምላክህ እምላለሁ!”+
እንዲሁም “ሕያው በሆነው በቤርሳቤህ መንገድ+ እምላለሁ!” የሚሉ ሰዎች፣
ይወድቃሉ፤ ዳግመኛም አይነሱም።’”+
9 ይሖዋን ከመሠዊያው በላይ ቆሞ አየሁት፤+ እሱም እንዲህ አለ፦ “የዓምዱን አናት ምታ፤ መሠረቶቹም ይናወጣሉ። አናታቸውን ቁረጥ፤ የቀሩትንም በሰይፍ እገድላቸዋለሁ። የሚሸሽ ሁሉ አያመልጥም፤ ለማምለጥ የሚሞክርም ሁሉ አይሳካለትም።+
3 ቀርሜሎስ አናት ላይ ቢደበቁም
ፈልጌ ከዚያ አወጣቸዋለሁ።+
ወደ ታችኛው የባሕር ወለል ወርደው ራሳቸውን ከዓይኔ ቢሰውሩም
በዚያ እባቡ እንዲነድፋቸው አዘዋለሁ።
5 ሉዓላዊው ጌታ፣ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ፣ አገሪቱን* ይነካልና፤
እሷም ትቀልጣለች፤+ በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ለሐዘን ይዳረጋሉ፤+
ምድሪቱ በሙሉ እንደ አባይ ወደ ላይ ትነሳለች፤
በግብፅ እንዳለውም የአባይ ወንዝ ተመልሳ ወደ ታች ትወርዳለች።+
7 ‘የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች* አይደላችሁም?’ ይላል ይሖዋ።
8 ‘እነሆ፣ የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ ዓይኖች በኃጢአተኛው መንግሥት ላይ ናቸው፤
እሱም ከምድር ገጽ ያጠፋዋል።+
ይሁንና የያዕቆብን ቤት ሙሉ በሙሉ አልደመስስም’+ ይላል ይሖዋ።
9 ‘እነሆ፣ እኔ ትእዛዝ እሰጣለሁና፤
ሰው እህልን በወንፊት እንደሚነፋና
አንዲትም ጠጠር ወደ ምድር እንደማትወድቅ ሁሉ
የእስራኤልንም ቤት በብሔራት ሁሉ መካከል እነፋለሁ።+
10 “ጥፋት አይደርስብንም ወይም ወደ እኛ አይጠጋም” የሚሉ
በሕዝቤ መካከል ያሉ ኃጢአተኞች ሁሉ በሰይፍ ይሞታሉ።’
11 ‘በዚያ ቀን የፈረሰውን የዳዊትን ዳስ አቆማለሁ፤+
በግንቡ ላይ ያሉትን ክፍተቶች እጠግናለሁ፤*
ፍርስራሾቹንም አድሳለሁ፤
በጥንት ዘመን እንደነበረው ዳግም እገነባዋለሁ፤+
12 በመሆኑም ከኤዶምና ስሜ ከተጠራባቸው ብሔራት ሁሉ የቀረውን ይወርሳሉ’+
ይላል ይህን የሚያደርገው ይሖዋ።
13 ‘እነሆ፣ እንዲህ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ፤
‘አራሹ አጫጁ ላይ ይደርስበታል፤
ዘሪውም ወይን ጨማቂው ላይ ይደርስበታል፤+
ተራሮችም ጣፋጭ የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፤+
14 ከሕዝቤ ከእስራኤል የተማረኩትን ሰዎች መልሼ እሰበስባለሁ፤+
እነሱም የወደሙትን ከተሞች መልሰው በመገንባት ይኖሩባቸዋል፤+
የወይን ተክል ተክለው የወይን ጠጁን ይጠጣሉ፤+
አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።’+
“ሸክም መሆን” ወይም “ሸክም መሸከም” የሚል ትርጉም አለው።
ወይም “ወንጀል።”
ቃል በቃል “በትረ መንግሥቱን የያዘውን።”
ቃል በቃል “በትረ መንግሥቱን የያዘውንም።”
ወይም “ወንጀል።”
ቃል በቃል “ፈራጅ የሆነውን።”
ወይም “መመሪያ፤ ትምህርት።”
ብር የተባለውን ማዕድን ያመለክታል።
ወይም “ቤተ መቅደስ።”
ወይም “ነፍሱን።”
ወይም “ነፍሱን።”
ወይም “ልበ ሙሉ።”
ወይም “በቀጠሮ ሳይገናኙ።”
“ወጥመድ ላይ የሚደረግ ምግብ ሳይኖር” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “የሰወረውን ጉዳይ።”
ወይም “በደማስቆ ድንክ አልጋ።”
ወይም “በያዕቆብ ቤት ላይ መሥክሩ።”
ወይም “ወንጀል።”
“ብዙ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ጌቶቻችሁንም።”
ወይም “ዓምፁ።”
ወይም “አንድ አሥረኛችሁን።”
ወይም “የምትበሉት ምግብ አልሰጠኋችሁም።” ቃል በቃል “ጥርሳችሁን አጠራሁ።”
ወይም “እንደ ሐዘን እንጉርጉሮ።”
“ምትሃታዊ ድርጊት የሚፈጸምባት ቦታ ትሆናለች” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “መራራነት።”
በቶረስ ኅብረ ከዋክብት የታቀፉ ፐልያዲስ የሚባሉ ከዋክብት ሊሆኑ ይችላሉ።
የኦርዮን ኅብረ ከዋክብት ሊሆን ይችላል።
ወይም “የመሬት ቀረጥ።”
ወይም “ወንጀላችሁ።”
ወይም “መረጃን ለመደበቅ የሚሰጥ ገንዘብ።”
እነዚህ ጣዖታት እንደ አምላክ ይመለክ የነበረውን የሳተርንን ፕላኔት ሊያመለክቱ ይችላሉ።
ወይም “ዘና ብለው።”
የይሁዳንና የእስራኤልን መንግሥታት የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ቃል በቃል “ወንበር።”
ወይም “ወይፈኖችን።”
ወይም “ባለ አውታር መሣሪያ።”
ወይም “በነፍሱ።”
ቃል በቃል “የአባቱ ወንድም።”
ወይም “መራራነት።”
ቃል በቃል “ለራሳችን ቀንዶች ወስደን የለም?”
ወይም “ከሃማት መግቢያ።”
የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
በጥርና በየካቲት የሚዘራውን እህል ያመለክታል።
ወይም “በዚህ ተጸጸተ።”
ወይም “በዚህ ተጸጸተ።”
እዚህ ላይ የተጠቀሰው የዮአስ (የኢዮዓስ) ልጅ የሆነው ዳግማዊ ኢዮርብዓም ነው። አሞጽ 1:1ን ተመልከት።
ወይም “የሾላ ፍሬዎችን የምወጋ።”
የበጋ ፍሬ በዋነኝነት የሚያመለክተው “በለስን” ሲሆን “ቴምርንም” ሊጨምር ይችላል።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ምድሪቱ።”
ወይም “ወደ ሐዘን እንጉርጉሮ።”
ወይም “ፀሐይ መውጫ።”
ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ምድሪቱን።”
ወይም “ክብ ጣሪያ፤ ባለ ቅስት ጣሪያ።”
ወይም “ለእኔ እንደ ኩሽ ልጆች።”
ወይም “ክፍተቶቻቸውን እጠግናለሁ።”
ቃል በቃል “ኮረብቶችም ሁሉ ይቀልጣሉ።”