የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • nwt 2 ዮሐንስ 1-13
  • 2 ዮሐንስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • 2 ዮሐንስ
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ዮሐንስ

የዮሐንስ ሁለተኛው ደብዳቤ

1 ከሽማግሌው፣ ለተመረጠችው እመቤትና* ለልጆቿ፦ ከልብ እወዳችኋለሁ፤ እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን ያወቁ ሁሉ ይወዷችኋል፤ 2 የምንወዳችሁ በውስጣችን በሚኖረው እውነት የተነሳ ነው፤ ይህም እውነት አብሮን ለዘላለም ይኖራል። 3 አባት ከሆነው አምላክና የአብ ልጅ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ እውነትንና ፍቅርን ጨምሮ ጸጋ፣ ምሕረትና ሰላም እናገኛለን።

4 ከልጆችሽ መካከል አንዳንዶቹ ከአብ በተቀበልነው ትእዛዝ መሠረት በእውነት እየተመላለሱ መሆናቸውን ስላወቅኩ እጅግ ደስ ብሎኛል።+ 5 ስለሆነም እመቤት ሆይ፣ እርስ በርስ እንዋደድ ዘንድ እለምንሻለሁ። (እየጻፍኩልሽ ያለሁት አዲስ ትእዛዝ ሳይሆን ከመጀመሪያ ጀምሮ የተቀበልነው ነው።)+ 6 ፍቅር ሲባል ደግሞ በትእዛዛቱ መሠረት መመላለስ ማለት ነው።+ እናንተ ከመጀመሪያ እንደሰማችሁት ትእዛዙ በፍቅር መመላለሳችሁን እንድትቀጥሉ ነው። 7 ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መምጣቱን+ አምነው የማይቀበሉ ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ወጥተዋልና።+ እንዲህ ያለ ሰው አሳችና ፀረ ክርስቶስ ነው።+

8 ሙሉ ሽልማት እንድታገኙ እንጂ የደከምንባቸውን ነገሮች እንዳታጡ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።+ 9 ከክርስቶስ ትምህርት አልፎ የሚሄድና በትምህርቱ ጸንቶ የማይኖር ሁሉ አምላክ የለውም።+ በዚህ ትምህርት ጸንቶ የሚኖር ሰው ግን አብና ወልድ አሉት።+ 10 ማንም ሰው ወደ እናንተ ቢመጣና ይህን ትምህርት ይዞ ባይመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት+ ወይም ሰላም አትበሉት። 11 ሰላም የሚለው ሰው የክፉ ሥራው ተባባሪ ይሆናልና።

12 የምነግራችሁ ብዙ ነገር ቢኖረኝም በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልፈልግም፤ ከዚህ ይልቅ ደስታችሁ የተሟላ እንዲሆን ወደ እናንተ መጥቼ ፊት ለፊት እንደማነጋግራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።

13 የተመረጠችው የእህትሽ ልጆች ሰላምታ ያቀርቡልሻል።

“ለተመረጠችው እመቤት” የሚለው አገላለጽ አንዲትን ሴት ወይም በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረን የክርስቲያን ጉባኤ ሊያመለክት ይችላል።

    የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ