የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w94 11/15 ገጽ 8-9
  • የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ ፖላንድ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ ፖላንድ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሐሰትን በድፍረት ማጋለጥ
  • ‘ከፍሬያቸው’
  • የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ ታይላንድ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • የይሖዋ ምስክሮች በዓለም ዙሪያ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ—ሕንድ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
w94 11/15 ገጽ 8-9

የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ ፖላንድ

በ1989 የበልግ ወራት ከቦልቲክ አገሮች አንሥቶ እስከ ጥቁር ባሕር ድረስ ያሉት የኮሙኒስት መንግሥታት መፈረካከስ ጀመሩ። የብረት መጋረጃው እየተሰባበረ ሲሄድ የምሥራቅ አውሮፓ አገሮችም የየራሳቸውን ነፃ ብሔራት ለመመሥረት ጥረት ማድረግ ጀመሩ። እጅግ ብዙ ኮረብቶች፣ ለጥ ያሉ ሜዳዎችና ወጣ ገባ ተራሮች ያሉባት ፖላንድ ከነዚህ አገሮች አንዷ ናት።a

የፖላንድ ሕዝብ ጠንካራ ሠራተኛ ነው። እንዲሁም ፖላንድ በዓለም የታወቁ አርቲስቶችንና ሳይንቲስቶችን አፍርታለች። ከዚህም በላይ በአሁኑ ጊዜ ቁጥሩ እየጨመረ የሚሄድ የአምላክ መንግሥት ምሥራች አዋጅ ነጋሪ የሆነ ሠራዊት አላት።

ሐሰትን በድፍረት ማጋለጥ

ፖላንድ ውስጥ እውነትን ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመማር የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች አሉ። አንዳንዶቹን ግን ዘመዶቻቸው ወይም ጎረቤቶቻቸው እውነትን እንዳይማሩ ይከለክሏቸዋል። ለምሳሌ ቮርትስላቭ በምትባል ከተማ አቅራቢያ ቀደም ሲል ፍላጎት አሳይታ የነበረች አንዲት ሴት በቤተሰቦቿና በጓደኞቿ ተፅዕኖ ምክንያት ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናቷን ታቆማለች። በአሥራዎቹ ዕድሜዋ ውስጥ የምትገኘው ልጅዋ ግን በመጠበቂያ ግንብ እትሞች ላይ በተከታታይ የወጡ የሐሰት ሃይማኖትን የሚያጋልጡ ርዕሶች አነበበች። ያነበበችው ነገር ለእውነት ፍላጎት አሳደረባት።

ከስድስት ወራት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በኋላ ይህች ልጅ ከሐሰት ሃይማኖት ጋር ያላትን ማንኛውንም ትስስር ለመበጠስ ፈለገች። ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደችና ውሳኔዋን ለቄሱ አሳወቀች። እርሳቸውም “እኔ ኬ—— ፒ——፣ የካቶሊክን እምነት የካድኩ መሆኔን አሳውቃለሁ” ብላ እንድትጽፍ ነገሯት።

በሚቀጥለው እሑድ ይህ መግለጫዋ በቤተ ክርስቲያን ተነበበ። የልጅቷ አያት ይህንን ሲሰሙ ራሳቸውን ሳቱ፤ ሴት አያቷም አለቀሱ። ሌሎቹ ምእመናን ግን “በመጨረሻ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ብዙ የሐሰት ድርጊቶች እንደሚፈጸሙ በግልጽ የተናገረች አንዲት ደፋር ተገኘች” አሉ። ይህች ደፋር ወጣት አሁን የተጠመቀች መንፈሳዊት እኅት ስትሆን በምትኖርበት አካባቢም ሰባት ጥናቶችን ለማስጀመር በቅታለች።

‘ከፍሬያቸው’

ኩያቨ ኤይ ፖሞዤ የተባለው ሳምንታዊ መጽሔት “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ” በሚል ርዕስ አንድ ዘገባ አውጥቶ ነበር። ጽሑፉ በከፊል እንዲህ ይላል፦ የሕዝበ ክርስትና ምእመናን “የሚያምኑባቸውን ሃይማኖታዊ መመሪያዎች በቁም ነገር አይዟቸውም። የሚናገሩትን ነገር (ደግሞም የሚናገሩት የመጽሐፍ ቅዱስን ትእዛዛት ነው) ተግባራዊ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች ግን ከነሱ እጅግ የተለዩ ናቸው።”

የምሥክሮቹን ሁኔታ በስም ክርስቲያን ከሆኑት ሰዎች ጋር በማነጻጸር ከገለጸ በኋላ ዘገባው እንዲህ በማለት ይቀጥላል፦ “እነዚህኛዎቹ የሃይማኖታቸውን ዋና ዋና እውነቶችና መሠረታዊ ሥርዓቶች አያውቋቸውም፤ በተግባርም አያውሏቸውም። . . . የይሖዋ ምሥክሮች ግን በአቋማቸው ሁሉ የሚናገሩትና የሚያደርጉት ነገር የሚስማማ መሆኑን በግልጽ ያሳያሉ፤ ይህም እነሱ ‘የሐሰት ነቢያት’ ሳይሆኑ በፍሬያቸው ሊታወቁ የሚገባቸው ሰዎች መሆናቸውን ያረጋግጣል። ‘ከእሾህ ወይን፣ ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?’ (ማቴዎስ 7:15–20)”

አንዲት ሴት ልጅዋ የካቶሊክን ቤተ ክርስቲያን ትቶ የይሖዋ ምሥክር በመሆኑ እንዳዘነች በመግለጽ ፕቺአቹካ ለተባለ አንድ ሳምንታዊ መጽሔት ደብዳቤ ጻፈች። ታዲያ የመጽሔቱ አዘጋጅ ምን ምክር ሰጠቻት? “ልጅሽ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መሰብሰብ ከጀመረና የሚያምኑበትን ነገር ተምሮ ከተቀበለው ይህ የራሱ ውሳኔ ነው፤ ይህም ውሳኔው ሊታወቅለትና ሊከበርለት ይገባል። . . . ይህ የሃይማኖት ቡድን በኅብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው በጣም ብዙ ጥሩ ጥሩ ጠባዮች የሚያሳዩ ሰዎች ያሉበት በመሆኑ ተለይቶ ይታወቃል፤ እነሱ አንድነት ያላቸውና በጠበቀ ፍቅር የተሳሰሩ፣ እጅግ ታማኞችና የማኅበረሰቡን ሥርዓትና ደንብ በሚገባ የሚጠብቁ እንዲሁም ከሚያስተምሩት እውነት ጋር ተስማምተው ለመኖር የቻሉ፣ ከፍ ተደርገው የሚታዩ የሥነ ምግባር ሕግጋትን የሚከተሉ ናቸው። እነዚህ ደግሞ ውድ ባሕርያት ናቸው።”

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ለተጨማሪ ማብራሪያ የ1994ን የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ ተመልከት።

[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

የአገሪቱ ሪፖርት መግለጫ

የ1993 የአገልግሎት ዓመት

የምሥክሮቹ ከፍተኛ ቁጥር፦ 113,551

ከሕዝቡ ብዛት ጋር ሲነፃፀር፦ 1 ምሥክር ለ339 ሰዎች

የመታሰቢያው በዓል ተሰብሳቢዎች፦ 235,642

የአቅኚዎች ብዛት በአማካይ፦ 7,961

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች በአማካይ፦ 79,131

የተጠማቂዎች ብዛት፦ 8,164

የጉባኤዎች ብዛት፦ 1,397

ቅርንጫፍ ቢሮው የሚገኝበት ቦታ፦ ናዳርዝይን

[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በሎድዝ የሚገኘው የፖላንድ ቅርንጫፍ ቢሮ በ1948

[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በቀድሞዋ ምሥራቅ ፕሩሲያ አርማ በመያዝ የተደረገ ሰልፍ፣ ሰኔ 1948

[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ሰባ ሁለቱ የፖላንድ ቤቴል አባሎች፣ ጥር 1993

[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በናዳርዝይን ያለው አዲሱ ቅርንጫፍ ቢሮ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ