በክርስቶስ ትንቢቶች ላይ እንዲያተኩሩ ሌሎችን አነሳሱ
1 በማቴዎስ 5:14 ላይ ተመዝግቦ እንደሚገኘው ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ” ብሏቸዋል። የኢየሱስ ተከታዮች ስለ ይሖዋ መንግሥት የሚገልጹትን ትንቢቶችና በክርስቶስ በኩል እኛን ለማዳን ስላደረገው ፍቅራዊ ዝግጅት በየትኛውም ስፍራ ለሚገኙ ሰዎች መናገር ነበረባቸው። ይህን ተልእኮ በአእምሮአችን በመያዝ በታኅሣሥ ወር ራእይ— ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት እንፈልጋለን።
2 ሰዎች ራእይ መደምደሚያው የተባለውን መጽሐፍ አንብበው መረዳት ይከብዳቸዋልን? ብዙዎች ያን ያህል ከባድ ሆኖ አላገኙትም። የመጽሐፉ አንባቢዎች ከሰጧቸው በርካታ አስተያየቶች ውስጥ ጥቂቶቹን ልብ በሉ። አንድ ሰው “ትምህርቱ ኃይለኛ ነው። ሆኖም ደስ ይላል። ወድጄዋለሁ” በማለት ተናግሯል። አንድ ቄስ “ከዚህ መጽሐፍ የበለጠ እውነተኛና የሚያስደስት መጽሐፍ በጭራሽ አይቼ ወይም አንብቤ አላውቅም” ብለዋል። ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መጽሐፉን አንብቦ የጨረሰ አንድ ግለሰብ “አሁን ዓይኖቼ ለእውነት በደንብ ተከፍተዋል። ጠቅላላ ሕይወቴን መለወጥ እፈልጋለሁ” ሲል አስተያየቱን ሰንዝሯል። ብዙዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆነውን የራእይ መጽሐፍ በሕይወታቸው ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በማስተዋል ሲያነቡና ትእዛዞቹን መጠበቅ ሲጀመሩ ደስታ እንዳገኙ ግልጽ ነው።
3 ብዙዎች ከቤት ወደ ቤት ከሚደረገው አገልግሎት በተጨማሪ ራእይ መደምደሚያው የተባለውን መጽሐፍ ለዘመዶቻቸው፣ ለሚያውቋቸው ሰዎችና በሥራ ምክንያት ለሚያገኟቸው ሰዎች መደበኛ ባልሆነ መንገድ በማበርከት የተሳካ ውጤት አግኝተዋል። ሕያው ከሆኑ ሥዕላዊ መግለጫዎቹ፣ ከጠቃሚ ሠንጠረዞቹና ለማስተማር ከሚረዱ በመጽሐፉ ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች ነገሮች አንተ በግል እንዴት እንደተጠቀምክ ግለጽ።
4 ከዚህ ጋር የሚመሳሰል ሐሳብ መግለጽ ትፈልግ ይሆናል:-
◼ “ሞቅ ያለ ሰላምታ። . . . እባላለሁ። ሕይወት በችግሮች የተሞላ ቢሆንም ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብሩህ አመላካከት እንዲኖሮት አንድ ነገር ልናካፍልዎት ነው የመጣነው። በዚህ በራእይ 1:3 ላይ ያሉትን የኢየሱስ ቃላት ያስተውሉ። [አንብበው።] ከነዚህ ትንቢቶች መካከል አንዱን የሚያሳየውን ሥዕላዊ መግለጫ ላሳይዎት። [ገጽ 302ን ገልጠህ አሳየውና በገጽ 303 ላይ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ማለትም ራእይ 21:3, 4ን በቀጥታ ከመጽሐፉ አንብብ።] ይበልጥ ደስተኛ እንዲሆኑ ራእይን ጥቅስ በጥቅስ የሚያብራራውን ይህን ግሩም መጽሐፍ እናበረክትልዎታለን። በተጨማሪም ሌላ ጊዜ መጥተን እነዚህን በጣም አስፈላጊ ትንቢቶች እንዲያስተውሉ ብንረዳዎት ደስ ይለናል።”
5 ሌሎች አቀራረቦችም እነሆ:-
◼ “እኔ [ስምህን ግለጽ] እና ጓደኛዬ [ስሙን ግለጽ] ሰዎችን የራእይ መጽሐፍ የሚገባ እንዲሆን ታስቦ የተጻፈ ነው ወይስ እነዚህ ትንቢቶች ለዘላለም ምሥጢር ሆነው የሚኖሩ ይመስላችኋል? እያልን እየጠየቅናቸው ነው። [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ብዙዎች እንደ እርሶ ያለ አመለካከት አላቸው። እዚህ በራእይ 1:3 ላይ ኢየሱስ የተናገረውን ልብ ይበሉ። [አንብበው።] ስለዚህ እነዚህ ትንቢቶች ሰው እንዲረዳቸው ታስበው የተጻፉ ናቸው። ለምሳሌ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት መግለጫዎች አንዱ በራእይ 14:6, 7 ላይ የሚገኘው ነው። [አንብበው።] ስለ ፍርዱ [ስለ ታላቂቱ ጋለሞታ በሥዕል የሚገልጸውን ገጽ 241 ግለጥ] እና ስለ በረከቶቹ [308 እና 309ን ግለጥ] የሚገልጹትን ሁለት ሥዕሎች ይመልከቱ። የራእይን መጽሐፍ ለመረዳት የሚያስችልዎትን ይህን መጽሐፍ ሊውሰዱ ይችላሉ።”
◼ “[ሰላምታ።] በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ስለሚፈጸሙት ነገሮች ትርጉም ከእርስዎ ጋር ለጥቂት ደቂቃዎች ለመወያየት ነው የመጣነው። ኑሮ እየተሻሻለ ሳይሆን ይበልጥ እየከፋ እንደመጣና ሥቃይና ክፋት በየትኛውም የምድር ክፍል እንደሚገኝ እንደተገነዘቡ አያጠራጥርም። [ትንሽ ቆም በል።] እስቲ ይህን ሥዕል ይመልከቱ። [ገጽ 180 እና 181ን ግለጥ።] የዚህ ሥዕል ትርጉም ምን እንደሆነ ባጭሩ ላሳይዎት? [ራእይ 12:7–9, 12ን ቀጥታ ከመጽሐፉ አንብብ፤ ከዚያም ሰይጣን ወደ ምድር መጣሉ ያስከተለውን ውጤት በገጽ 182 ላይ ባሉት ሥዕሎች አማካኝነት አሳየው።] ይህ የተፈጸመ ክስተት ሲሆን አሁን የምንኖረውም ሰይጣን የሚጠፋበት ጊዜ በተቃረበበት ወቅት ነው። ይህን ግሩም መጽሐፍ ወስደው ስለዚህ ጉዳይ ይበልጥ ለማወቅ ይችላሉ።”
6 ውጤት የሚያስገኙት አቀራረቦች የምናነጋግረውን ሰው የሚያሳስበውን ማለትም የሚያስፈልገው ወይም ሊጠቀምበት የሚችል ነገር እንደሆነ በግልጽ የሚጠቁሙት ናቸው። በውይይትህ ወቅት የምታነጋግረው ሰው “ይህ እኔን ይመለከተኛል” የሚል ግንዛቤ እንዲኖረው እርዳው። አንድን አቀራረብ ስንዘጋጅ ‘በክልሌ ውስጥ ያሉት ሰዎች በጣም የሚያሳስቧቸው ጉዳዮች ምንድን ናቸው? ምን ችግሮች አሉባቸው? ይሖዋ ችግሮቻቸውን እንደሚረዳ በሚያሳይ መንገድ መልእክቱን ማቅረብ የምችለው እንዴት ነው?’ እያልን ራሳችንን መጠየቅ አለብን።
7 በተመላልሶ መጠየቅ ልትረዳቸው እንድትችል ያሳዩትን ፍላጎትና ያበረከትክላቸውን ጽሑፎች መመዝገብህን አትርሳ። አሁን ጊዜው ሳያልቅ ቅን ልብ ያላቸውን ሰዎች በቅንዓት በመፈለግ የአዳኛችን የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች እንዲሆኑ እንርዳቸው።— ማቴ. 16:24