ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ውጤታማ በሆነ መንገድ ማስተዋወቅ
1 ኢየሱስ በመግቢያ አጠቃቀሙ የተካነ ነበር። የሰዎችን ፍላጎት ለመቀስቀስ ምን ማለት እንዳለበት ያውቅ ነበር። በአንድ ወቅት የሚጠጣ ውኃ እንድትሰጠው በመጠየቅ ብቻ ከአንዲት ሳምራዊት ጋር ውይይት ከፈተ። ‘አይሁዶች ከሳምራውያን ጋር ስለማይተባበሩ’ ይህ ወዲያውኑ ትኩረቷን ሳበው። ቀጥሎ ያደረጉት ውይይት እሷንና ሌሎች ብዙ ሰዎችን አማኞች እንዲሆኑ ረድቷቸዋል። (ዮሐ. 4:7–9, 41) ከእሱ ምሳሌ መማር እንችላለን።
2 ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ለማበርከት ስትዘጋጅ ራስህን ‘በአግልግሎት ክልላችን ያሉትን ሰዎች በጣም የሚያሳስቧቸው ነገሮች የትኞቹ ናቸው? በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ለሚገኝ፣ በዕድሜ ለገፋ ሰው፣ ለባል ወይም ለሚስት ማራኪ ሊሆን የሚችለው የቱ ነው?’ እያልክ ጠይቅ። ከአንድ በላይ የሆኑ መግቢያዎችን ልትዘጋጅና ለሁኔታው ይበልጥ የሚስማማውን ልትጠቀም ትችላለህ።
3 የቤተሰብ ሕይወት እያዘቀጠ መምጣቱ ብዙዎችን ስለሚያሳስባቸው እንዲህ ልትል ትችላለህ:-
◼ “ዛሬ አንድ በጣም የሚጠቅም ነገር ለማሳየት ቤተሰቦችን እየጠየቅን ነው። በየዕለቱ የሚያጋጥሙ የኑሮ ጭንቀቶች ዛሬ ባሉ ቤተሰቦች ላይ ከባድ ውጥረቶችን ፈጥረዋል። ከእነዚህ ጭንቀቶች ለመላቀቅ የሚያስችል እርዳታ ሊያገኙ የሚችሉት ከየት ነው? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ ሊረዳን ይችላል። [2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17ን አንብብ።] ቅዱሳን ጽሑፎች ቤተሰብ እንዳይፈርስ የሚረዱ ጠቃሚ መመሪያዎችን ያቀርባሉ። በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ በተባለው በዚህ መጽሐፍ ላይ በገጽ 238 አንቀጽ 3 ላይ የተገለጸውን ሐሳብ ልብ ይበሉ።” አንቀጽ 3ን አንብብና መጽሐፉን አበርክት።
4 በአካባቢው የተላለፈውን ዜና የምትጠቀም ከሆነ እንዲህ ልትል ትችላለህ:-
◼ “ስለ [በአካባቢው አሳሳቢ የሆነውን ርዕስ ጥቀስ] የተነገረውን ዜና ሰምተዋል? ስለ ጉዳዩ ምን ይሰማዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ ዓለም ወዴት እያመራ እንዳለ ያጠያይቃል፤ አይደለም እንዴ? መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህ ነገሮች በመጨረሻዎቹ ቀናት እንደምንኖር የሚያሳዩ ማስረጃዎች እንደሆኑ አስቀድሞ ተናግሯል።” ከዚያም ለዘላለም መኖር የተባለው መጽሐፍ ገጽ 150–3 ላይ ያለውን ሐሳብ ተመልከት።
5 ብዙዎች እየጨመረ የመጣው ወንጀል ስላስከተለው ችግር ያስባሉ። “ማመራመር” በተባለው መጽሐፍ በገጽ 10 ላይ “ወንጀል/ደኅንነት” በሚለው ርዕስ ሥር የሚገኘውን የመጀመሪያውን መግቢያ ልትጠቀም ትችላለህ:-
◼ “ከሰዎች ጋር ስለ ግል ደኅንነታቸው እየተወያየን ነው። በአካባቢያችን ብዙ ወንጀል ይፈጸማል፤ ይህም ሕይወታችንን ሊነካ ይችላል። እንደ እኔና እርስዎ ያሉ ሰዎች በጨለማ ያለ ስጋት የምንጓዝበት ዘመን የሚመጣ ይመስልዎታል?” መዝሙር 37:10, 11 ልታነብና ለዘላለም መኖር ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 156–8 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ በመጠቀም የአምላክ መንግሥት ስለምታመጣቸው በረከቶች ልትገልጽ ትችላለህ።
6 ቀላል አቀራረብ የምትመርጥ ከሆነ “ማመራመር” በተባለው መጽሐፍ በገጽ 12 ከሚገኘው የላይኛው ክፍል ጋር የሚመሳሰል መግቢያ መጠቀም ትፈልግ ይሆናል:-
◼ “መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊቱን ጊዜ አስመልክቶ ስለያዘልን ተስፋ የሚናገረውን እንዲመረምሩ ጎረቤቶቻችንን እያበረታታን ነው። [ራእይ 21:3, 4ን አንብብ።] ይህ መልካም አይመስልዎትም? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] የዚህ መጽሐፍ 19ኛው ምዕራፍ ታዛዥ ሰዎች በአምላክ መንግሥት ሥር የሚያገኟቸውን ሌሎች በረከቶች ያጎላል።” ሰውዬው ፍላጎት ካሳየ ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ አበርክት።
7 ውጤታማ መግቢያ ማዘጋጀት ጽድቅ የተራቡ ሰዎችን ልብ ለመንካት እንድትችሉ ያደርጋችኋል።— ማቴ. 5:6