የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/96 ገጽ 1
  • ራሳችንን በፈቃደኝነት ማቅረብ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ራሳችንን በፈቃደኝነት ማቅረብ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለማንኛውም መልካም ሥራ ራሳችንን በፈቃደኝነት ማቅረብ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • አገልግሎትህን ማስፋት የምትችልባቸው መንገዶች
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
  • ማደግህ በግልጥ ይታይ
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
  • በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ያሉትን አስቧቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 12/96 ገጽ 1

ራሳችንን በፈቃደኝነት ማቅረብ

1 መዝሙራዊው ዳዊት የይሖዋ ሕዝቦች “ራሳቸውን በፈቃደኝነት ያቀርባሉ” ማለትም “በፈቃደኝነት ፈጣን ምላሽ ይሰጣሉ” በማለት ትንቢት ተናግሮ ነበር። (መዝ. 110:3 አዓት የግርጌ ማስታወሻ።) ይህ በዓለም አቀፉ የወንድማማች ማኅበራችን ውስጥ በትክክል እየተፈጸመ ነው። ባለፉት አራት የአገልግሎት ዓመታት የይሖዋ ሕዝቦች የመንግሥቱን ምሥራች ለማሰራጨት በየዓመቱ ከአንድ ቢልዮን የሚበልጥ ሰዓት አሳልፈዋል። በስብከቱና ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ ከመካፈላችን በተጨማሪ ሌሎች ሰዎችን ለመርዳት ራሳችንን በፈቃደኝነት ማቅረብ የምንችልባቸው ብዙ መስኮች አሉ።

2 ፈቃደኝነታችንን ልናሳይ የምንችልባቸው መስኮች፦ በጉባኤ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ሰዎች ወደ ስብሰባዎች እንዲመጡ መርዳት ያስፈልግ ይሆናል። ወደ ስብሰባ ይዘሃቸው ለመሄድ እንደምትፈልግ ለምን አትነግራቸውም? ሌሎች ደግሞ የታመሙ፣ አቅመ ደካማ የሆኑ ወይም ሆስፒታል የገቡ ሊሆኑ ይችላሉ። እነርሱን ለመጠየቅም ሆነ በአንድ ዓይነት መንገድ እርዳታህን ለመለገስ ቀዳሚ ልትሆን ትችላለህ? ማበረታቻ የሚያስፈልገው አንድ ግለሰብ ወይም አንድ ቤተሰብ ሊኖር ይችላል። እንደነዚህ ያሉ ሰዎችን በቤተሰብ ጥናትህ ላይ አልፎ አልፎ እንዲገኙ ለመጋበዝ አስበሃል? አንድ አቅኚ ወይም አንድ አስፋፊ አብሯቸው የሚያገለግል ሰው ይፈልጉ ይሆናል። በአገልግሎት አብረሃቸው ለማገልገል ለምን ራስህን አታቀርብም? እነዚህ በእምነት ለሚዛመዱን ሰዎች በፈቃደኝነት ተነሳስተን መልካም ነገሮችን የምናደርግባቸው ጥቂት መስኮች ናቸው።— ገላ. 6:10

3 ወንድሞች ለሽማግሌዎችና ለጉባኤ አገልጋዮች የወጡትን ብቃቶች ለማሟላት በመጣጣር በይሖዋ ድርጅት ውስጥ ያላቸውን ችሎታ በመጠቀም ፈቃደኝነታቸውን ማሳየት ይችላሉ። (1 ጢሞ. 3:2-10, 12, 13፤ ቲቶ 1:5-9) በቁጥር እያደግን ስንሄድ በስብከቱና በማስተማሩ እንዲሁም ጉባኤዎችን በእረኝነት በመጠበቁ ሥራ ቅድሚያ ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆኑ ብቃት ያላቸው ወንድሞች ያስፈልጋሉ።— 1 ጢሞ. 3:1

4 ምናልባት አንዳንዶቻችን አልፎ አልፎ ረዳት አቅኚ በመሆን በይሖዋ አገልግሎት ውስጥ ያለንን ተሳትፎ ለማስፋት ራሳችንን ማቅረብ እንችል ይሆናል። በተጨማሪም በፕሮግራማችን ላይ ምክንያታዊ የሆኑ ጥቂት ማስተካከያዎችን በማድረግ ላልተወሰነ ጊዜ ረዳት አቅኚ ሆነን ለማገልገል ወይም ዘወትር አቅኚ ለመሆን እንችል ይሆናል። ሁኔታዎቻችን የበለጠ እርዳታ ወደሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ሄደን ለማገልገል የሚያስችሉን ናቸው? በዓለም ዙሪያ በሚደረገው ጭማሪ በቀጥታ አስተዋጽኦ ለማድረግ በቤቴል ለማገልገል ራሳችንን ማቅረብ እንችላለን? በዓለም ዙሪያ የመንግሥት አዳራሾች፣ ትላልቅ ስብሰባ የሚደረግባቸው አዳራሾችና ቅርንጫፍ ቢሮዎች በብዛት እየተገነቡ ነው። ለዚህ የግንባታ ሥራ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች በእጅጉ ያስፈልጋሉ። ለእነዚህ መልካም ሥራዎች ራሳቸውን በፈቃደኝነት ያቀረቡ ሁሉ በጣም የሚደነቁ ከመሆናቸውም በላይ የተትረፈረፉ በረከቶች ያገኛሉ!— ሉቃስ 6:38

5 እነዚህ ጊዜያት በደስታ የሚያስፈነድቁ ናቸው። ይሖዋ በመንፈሱ አማካኝነት ራሳቸውን በፈቃደኝነት ካቀረቡ ሕዝቦቹ ጋር ሆኖ በምድር ላይ አስደናቂ ሥራዎችን እያከናወነ ነው! ይሖዋ በድርጅቱ አማካኝነት በመንግሥት እንቅስቃሴ ውስጥ ለመካፈል የሚያስችል ግብዣ ባቀረበ ቁጥር ራሳችንን ‘አሁንም ራሴን በፈቃደኝነት እያቀረብኩ ነውን?’ ብለን ብንጠይቅ ጥሩ ይሆናል። ከዚያ በኋላ ልባችንንና ሁኔታዎቻችንን በጸሎት መመርመር ይኖርብናል። ለአምላክ ያደርን መሆናችን የቻልነውን ያህል በቅዱስ አገልግሎት በመካፈል የይሖዋን ልብ እንድናስደስት ይገፋፋናል!— ሶፎ. 3:17

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ