የአቀራረብ ናሙናዎች
በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ
“አንዳንድ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ አስተማማኝ ትንቢት የያዘ መጽሐፍ እንደሆነ ያምናሉ። ሌሎቹ ግን ግልጽ ያልሆኑና በተለያየ መንገድ ሊተረጎሙ የሚችሉ ትንቢቶችን የያዘ መጽሐፍ እንደሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ?” ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። የጥር 1ን መጠበቂያ ግንብ ለቤቱ ባለቤት ስጠውና ገጽ 16 ላይ በሚገኘው በመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ያለውን ሐሳብ አብራችሁ ተመልከቱ፤ በተጨማሪም ቢያንስ አንድ ጥቅስ አንብቡ። መጽሔቶቹን እንዲወስድ ከጋበዝከው በኋላ በቀጣዩ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
ጥር 1 መጠበቂያ ግንብ
“በጥንት ዘመን ከኖሩ ታላላቅ ወንዶችና ሴቶች ብዙ ትምህርት ማግኘት እንችላለን። እርስዎ በዚህ አባባል ይስማማሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ጥቅስ ስለ አንድ ታላቅ ሰው ይኸውም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‘የአምላክ ወዳጅ’ ተብሎ ስለተጠራው ብቸኛው ሰው ይናገራል። [ያዕቆብ 2:23ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክ አብርሃምን እንደ ወዳጁ የቆጠረው ለምን እንደሆነና አብርሃም ከተወልን ምሳሌ ምን መማር እንደምንችል ያብራራል።”
ጥር ንቁ!
“ጉቦ፣ እጅ መንሻና ሌሎች ሐቀኝነት የጎደላቸው ድርጊቶች በንግዱ ዓለም ውስጥ የተለመዱ እየሆኑ መጥተዋል። አንዳንዶች በንግዱ ዓለም ስኬታማ ለመሆን በተወሰነ መጠንም ቢሆን ማጭበርበር የግድ አስፈላጊ እንደሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እስቲ ይህን ትኩረት የሚስብ ጥቅስ ይመልከቱ። [ምሳሌ 20:17ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ሐቀኛ መሆን ጠቃሚ የሆነው ለምን እንደሆነ ያብራራል።”