የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/15 ገጽ 2
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • ምሥራቹን የምንሰብክባቸው መንገዶች
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
  • ወዲያውኑ ተከታትላችሁ እርዷቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • ኢንተርኔት ከሚያስከትላቸው አደጋዎች መራቅ የሚቻለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—2005
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
km 7/15 ገጽ 2

የጥያቄ ሣጥን

◼ አስፋፊዎች በኢንተርኔት ተጠቅመው በውጭ አገር ለሚኖሩ የማያውቋቸው ሰዎች ምሥክርነት መስጠት ወይም እነሱን ማስጠናት ይኖርባቸዋል?

አንዳንድ አስፋፊዎች ሥራችን በታገደበት ወይም ጥቂት አስፋፊዎች ብቻ ባሉበት አገር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማግኘት በኢንተርኔት ይጠቀማሉ። እንዲህ ማድረግ ጥሩ ውጤት ያስገኘበት ጊዜ አለ። ይሁንና አስፋፊዎች ከማያውቁት ሰው ጋር በኢሜይል ወይም በቻት ሩም አማካኝነት ውይይት ማድረጋቸው አደጋ አለው። (የሐምሌ 2007 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3⁠ን ተመልከት።) ወንድሞችና እህቶች ዓላማቸው ቅን ልብ ላላቸው ሰዎች የመንግሥቱን መልእክት ማዳረስ ቢሆንም እንዲህ ያለ ውይይት ማድረግ መጥፎ ጓደኝነት እንዲመሠርቱ ሊያደርግ ይችላል፤ አልፎ ተርፎም ከከሃዲዎች ጋር ሊገናኙ ይችላሉ። (1 ቆሮ. 1:19-25፤ ቆላ. 2:8) ከዚህም በተጨማሪ የመንግሥቱ ሥራ በታገደበት አገር የሚደረጉ የኢሜይል ልውውጦች በባለሥልጣናት ሊመረመሩ ይችላሉ። በመሆኑም እንዲህ ያሉ የመልእክት ልውውጦች በዚያ አገር ያሉ ወንድሞችንና እህቶችን ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል። ከዚህ አንጻር አስፋፊዎች በሌላ አገር የሚኖሩ ሰዎችን በኢንተርኔት አማካኝነት ፈልገው ምሥራቹን ለማካፈል ጥረት ማድረግ አይኖርባቸውም።

ከውጭ አገር ለመጣ ግለሰብ መደበኛ ባልሆነ መንገድ የመመሥከር አጋጣሚ ካገኘን ቅርንጫፍ ቢሮው መመሪያ ካልሰጠን በቀር ወደ አገሩ ከተመለሰ በኋላ ከእሱ ጋር መወያየታችንን መቀጠል የለብንም። ከዚህ ይልቅ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወይም በአካባቢው ካለው ቅርንጫፍ ቢሮ ጋር ለመገናኘት jw.orgን መጠቀም የሚችለው እንዴት እንደሆነ ልናሳየው እንችላለን። በተጨማሪም በአካባቢው ወዳለ የመንግሥት አዳራሽ እንዲሄድ ልናበረታታው እንችላለን። እርግጥ ነው፣ በአንዳንድ አገሮች የመንግሥት አዳራሾች ላይኖሩ ይችላሉ። ግለሰቡ በአካባቢው ያሉ የይሖዋ ምሥክሮችን ማግኘት ከፈለገ እባካችሁ ተከታትላችሁ እርዱት (S-43) የተባለውን ቅጽ ሞልተን ለጸሐፊው መስጠት እንችላለን፤ እሱ ደግሞ በjw.org አማካኝነት ይልከዋል። ፍላጎት ያሳየው ግለሰብ በሚኖርበት አካባቢ ያለውን ለየት ያለት ሁኔታ በደንብ የሚያውቀውና መንፈሳዊ እርዳታ ለመስጠት አመቺ ሁኔታ ላይ ያለው በዚያ አካባቢ ያለውን ሥራ የሚከታተለው ቅርንጫፍ ቢሮ ነው።—የሰኔ 2014 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 7⁠ን እና የኅዳር 2011 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 2⁠ን ተመልከት።

በአሁኑ ጊዜ እያወያየነው ያለ ሰው ወደ ሌላ አገር ከሄደ ወይም በኢንተርኔት አማካኝነት የተዋወቅነውና በአሁኑ ጊዜ የምናስጠናው በሌላ አገር የሚኖር ግለሰብ ካለ ከላይ ያሉትን መመሪያዎች መከተል ይኖርብናል። ይሁንና በአካባቢው ካሉ አስፋፊዎች ጋር እስኪገናኝ ድረስ ውይይታችንን መቀጠል እንችላለን። ይሁን እንጂ ግለሰቡ የሚኖረው ሥራችን በታገደበት አገር ከሆነ በደብዳቤ፣ በስልክና በሌሎች የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች አማካኝነት የመጽሐፍ ቅዱስ ውይይት ስናደርግ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን።—ማቴ. 10:16

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ