በብሮሹሮች መጠቀምን አትርሱ
ከቤት ወደ ቤት ወይም መደበኛ ባልሆነ መንገድ ስንመሰክር አብዛኛውን ጊዜ ውይይታችን ማራኪ ከሆኑት ብሮሹሮቻችን በአንዱ ላይ ተብራርቶ ወደነበረ ነጥብ ያመራል። በተለይ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን በምናበረክትበት በሚያዝያና በግንቦት እያንዳንዳችን ይህንን ጉዳይ በአእምሮአችን ልንይዘው ይገባል። በአገልግሎት ከምታበረክቷቸው መጽሔቶች ጋር ሁልጊዜ የተለያዩና በዛ ያሉ ብሮሹሮች አብራችሁ በመያዝ ለማበርከት ትችላላችሁ። በዚህም መንገድ ውጤታማ ምስክርነት ለመስጠት አስፈላጊው ትጥቅ ይኖራችኋል። በሚያዝያና በግንቦት ከምታበረክቷቸው መጽሔቶች ጋር ወይም በነሱ ምትክ (ትምህርት ቤት ከተባለው ብሮሹር በስተቀር) የፈለጋችሁትን ብሮሹር ይዛችሁ መሄድ ትችላላትሁ። — ከምሳሌ 15:23 ጋር አወዳድር።