የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/12 ገጽ 2
  • “ለሁሉም ዓይነት ሰዎች” ስበኩ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ለሁሉም ዓይነት ሰዎች” ስበኩ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ብሮሹሮች ለአገልግሎት ጠቃሚ የሆኑ መሣሪያዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • በብሮሹሮች መጠቀምን አትርሱ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • “የግለሰቡን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ የቆዩ መጽሔቶችን ወይም ብሮሹሮችን አበርክቱ”
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • ጎረቤቶቻችን ምሥራቹን መስማት ያስፈልጋቸዋል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
km 1/12 ገጽ 2

“ለሁሉም ዓይነት ሰዎች” ስበኩ

1. ውጤታማ ወንጌላውያን ከእጅ ባለሙያዎች ጋር የሚመሳሰሉት እንዴት ነው?

1 አንድ የተዋጣለት የእጅ ባለሙያ የተለያዩ መሣሪያዎች የሚኖሩት ከመሆኑም ሌላ እያንዳንዱን መሣሪያ መቼ እና እንዴት መጠቀም እንዳለበት ያውቃል። በተመሳሳይ እኛም የወንጌላዊነት ሥራችንን እንድንወጣ የሚያግዙን በርካታ መሣሪያዎች አሉን። ለምሳሌ ያህል፣ “ለሁሉም ዓይነት ሰዎች” መስበክ እንድንችል የሚረዱን የተለያዩ ብሮሹሮች ተዘጋጅተውልናል። (1 ቆሮ. 9:22) የዚህ ወር የመንግሥት አገልግሎታችን አንደኛው አባሪ ከእነዚህ ብሮሹሮች መካከል አንዳንዶቹን የያዘ ሲሆን እያንዳንዱ ብሮሹር ለማን ታስቦ እንደተዘጋጀና ብሮሹሩን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል ይገልጻል።

2. በአገልግሎታችን ላይ ብሮሹሮችን መጠቀም የምንችለው መቼ ነው?

2 ብሮሹሮቹን የምንጠቀመው መቼ ነው?፦ የእጅ ባለሙያው አንድን መሣሪያ አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ሁሉ ይጠቀምበታል። በተመሳሳይ እኛም አንድ ብሮሹር በሚበረከትበት ወር ብቻ ሳይሆን ለአንድ ሰው ሊጠቅመው ይችላል ብለን በምናስብበት ጊዜ ሁሉ ልናበረክትለት እንችላለን። ለምሳሌ ያህል፣ የምናገለግለው የክርስትና እምነት ባልተስፋፋበት ብሎም ሰዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ ያላቸው ፍላጎት አነስተኛ በሆነበት አካባቢ ከሆነ የሚበረከተው ጽሑፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለው መጽሐፍ ቢሆንም እንኳን ተስማሚ የሆነ ብሮሹር ማበርከታችን ጠቃሚ ነው፤ የግለሰቡን የማወቅ ፍላጎት ካነሳሳን በኋላ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ልናስተዋውቀው እንችላለን።

3. ለምሥክርነቱ ሥራ የሚረዱንን መሣሪያዎች በጥበብ መጠቀም ያለብን ለምንድን ነው?

3 መጽሐፍ ቅዱስ በሙያቸው ሥልጡን ስለሆኑ ሰዎች በአድናቆት ይናገራል። (ምሳሌ 22:29) በዛሬው ጊዜ “ቅዱስ” ከሆነው ‘ምሥራቹን የማወጅ ሥራ’ የበለጠ አስፈላጊ ሥራ እንደሌለ የተረጋገጠ ነው። (ሮም 15:16) “ምንም የሚያፍርበት ነገር እንደሌለው ሠራተኛ” ለመሆን ያሉንን መሣሪያዎች በጥበብ ለመጠቀም ጥረት እናደርጋለን።—2 ጢሞ. 2:15

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ