በሐምሌ ወር ውጤታማ በሆነ መንገድ በብሮሹሮች መጠቀም
1 ደቀ መዛሙርት የማድረጉን ሥራ ለማፋጠን ድርጅቱ ብዙ የተለያዩ ጽሑፎችን አትረፍርፎ ሰጥቶናል። ከእነዚህም መካከል አምላክ ለምድር ስላለው ዓላማ፣ ስለ ሥላሴ፣ ስለ አምላክ ስም፣ ስለ መንግሥቲቱ አስተዳደር፣ አምላክ ክፋትን ስለመፍቀዱና ስለመሳሰሉት ርእሰ ጉዳዮች የሚያብራሩ ብሮሹሮች ይገኙባቸዋል። በአገልግሎት ክልላችን ውስጥ ያሉትን ሰዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመርዳት በብሮሹሮች እንዴት ልንጠቀም እንችላለን?
2 አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የተባለው ብሮሹር ከመከራ ነፃ የሆነ አዲስ ዓለም መቅረቡን ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ያስረዳል። ብሮሹሩን እንዴት ብለን ልናስተዋውቅ እንችላለን? ምክንያቱን ማስረዳት በተባለው መጽሐፍ ላይ “መከራ” በሚለው ርእስ ስር ከገጽ 393 ጀምሮ የቀረቡትን ሐሳቦች ማግኘት ይቻላል፤ ወይም ደግሞ በገጽ 12 ላይ “የፍትህ መጓደል/መከራ” በሚለው ርእስ ስር ባሉት መግቢያዎች መጠቀም ልትመርጥ ትችል ይሆናል።
3 እንዲህ ልትል ትችላለህ፦
◼ ‘ሰዎች ስለሚደርስባቸው የፍትህ መጓደልና መከራ አምላክ በእርግጥ ያስባልን?’ ብለው አስበው ያውቃሉ?” መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። መዝሙር 72:12–14ን አንብብ። ከዚያም አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የተባለውን ብሮሹር ገጽ 22 ገልጠህ በክፍል 10 ውስጥ ጎላ ተደርገው የተጻፉትን ርዕሶች እንዲሁም በገጽ 23 ላይ ያለውን ሥዕል ትርጉም አወያየው። ብሮሹሩን መውሰድ እምቢ ካለ ለተጨነቁት የሚሆን ማጽናኛ ወይም ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት ወይም እነዚህን ከመሳሰሉት ትራክቶች አንዱን ለምን አታበረክትለትም?
4 ክርስቲያን ነኝ ብሎ ለሚናገር ሰው በሚከተለው አቀራረብ ልታነጋግረው ትችላለህ፦
◼ “በአካባቢያችን ያሉትን ሰዎች አንድ ጥያቄ እየጠየቅናቸው ነው። እርስዎም ያለዎትን አስተያየት ቢሰጡን ደስ ይለናል። ኢየሱስ የአምላክ መንግሥት እንድትመጣና ፈቃዱ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሆን ዘንድ እንድንጸልይ አስተምሮናል፤ ሆኖም በእርግጥ የአምላክ ፈቃድ በምድር ላይ ይፈጸማል ብለው ያስባሉን?” የቤቱ ባለቤት መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም መንግሥት የተባለውን ብሮሹር ገጽ 31ን አውጥተህ የቤቱ ባለቤት በራእይ 21:3, 4 ላይ የተገለጹትን ተስፋዎች እንዲያተኩርባቸው አድርግ። በብሮሹሩ በገጽ 29 ላይ በቀረቡት ነጥቦች ውይይቱን ልትቀጥል ትችላለህ። የአምላክ መንግሥት አስተዳደር የአምላክ ፈቃድ በምድር ላይ እንዲፈጸም የምታደርግ መሆኗን አብራራለት። የቤቱ ባለቤት ብሮሹሩን ካልተቀበለ ይህ ዓለም ከመጥፋት ይተርፍ ይሆን? የተባለውን ትራክት ልታበረክትለት ትችላለህ።
5 በአካባቢህ የወንጀል ፍርሃት ካለ የሚከተለው መግቢያ ተስማሚ ሊሆን ይችላል።
6 እንዲህ ልትል ትችላለህ፦
◼ “ብዙ ሰዎች ‘አምላክ ፍቅር ከሆነ ክፋትን ለምን ይፈቅዳል?’ ብለው ያስባሉ። እርስዎስ እንደዚህ ብለው አስበው ያውቃሉ?” የቤቱ ባለቤት አስተያየቱን እንዲሰጥ ፍቀድለትና ከዚያም እንዲህ በል:- “ሰዎች ለሚሠሯቸው መጥፎ ነገሮች አምላክን እንዳንወቅስ ምሳሌ 19:3 እንደሚያስጠነቅቀን ልብ ይበሉ።” ጥቅሱን ካነበብክ በኋላ “እነሆ፣ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” በተባለው ብሮሹር በገጽ 15 ላይ እንዲያተኩር በማድረግ አንቀጽ 27ን አንብብ። ይህም ቀጥሎ ባሉት አንቀጾች ላይ ወደ መወያየት ሊመራ ይችላል።
7 በብሮሹሮች ተጠቅሞ በግ መሰል የሆኑትን ሰዎች ስለ ምሥራቹ ማስተማር ሁላችንም ልናደርገው የምንችለው ነገር ነው። ከሁሉም በላይ በጣም አስፈላጊ በሆነው አገልግሎት መሳተፍ ለሚጀምሩ አዲሶች በሐምሌና በነሐሴ በብሮሹሮች መጠቀማቸው ጥሩ ዘዴ ይሆንላቸዋል። ልጆችም በመስክ አገልግሎት ውጤታማ በሆነ መንገድ በብሮሹሮችና በትራክቶች ሊጠቀሙ ይችላሉ። በማንኛውም የኑሮ ደረጃ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ ከአምላክ ድርጅት ጋር እንዲተባበሩ ልንረዳቸው እንችላለን። ወቅታዊ በሆኑት ብሮሹሮቻችን ውጤታማ በሆነ መንገድ እየተጠቀምን በስብከቱ እንቅስቃሴ መካፈሉ መብታችን ነው።