የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/95 ገጽ 2
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምሥራቹን ለማዳረስ በትራክቶች ተጠቀሙ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • በብሮሹሮች መጠቀምን አትርሱ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • መጽሔቶቻችንን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙባቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ጽሑፎቼ በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 3/95 ገጽ 2

የጥያቄ ሣጥን

◼ ለአገልግሎት ለምንጠቀምባቸው መሣሪያዎች ምን ትኩረት ልንሰጥ ይገባል?

1 አንድ የምሥራቹ አገልጋይ ተገቢ የሆነ ቅዱስ ጽሑፋዊ አቀራረብ በአእምሮው የያዘ ቢሆንም የሚጠቀምባቸውን መሣሪያዎች አላዘጋጀ ይሆናል። በር ላይ ሲደርስ በወቅቱ የሚበረከተውን ጽሑፍ አልያዘ ይሆናል። በአገልግሎት ቦርሳው ውስጥ ያሉት መጽሔቶች፣ ብሮሹሮችና ትራክቶች የተጨማደዱ ወይም የተሻሹ ሊሆኑ ይችላሉ። ቦርሳው በሚገባ ባለመደራጀቱ ምክንያት እርሳሱን ወይም ከቤት ወደ ቤት መመዝገቢያ ቅጹን ለማግኘት ይቸገር ይሆናል። ወደ መስክ አገልግሎት ከመውጣትህ በፊት የምትገለገልበትን መሣሪያ በጥንቃቄ ማየትህ በጣም አስፈላጊ ነው።

2 በሚገባ የተደራጀ የአገልግሎት ቦርሳ ምን ነገሮችን መያዝ አለበት? መጽሐፍ ቅዱስ በጣም አስፈላጊ ነው። ከቤት ወደ መመዝገቢያ ቅጾችን ጭምር ያዝ። በወሩ ውስጥ የሚበረከተውን ጽሑፍ መያዝህን አረጋግጥ። ወቅታዊ የመጽሔት እትሞችም ሆኑ ትራክቶችና ብሮሹሮች ያስፈልጋሉ። ማመራመር የተባለውን መጽሐፍ ያዝ። የወቅቱን የመንግሥት አገልግሎታችን እትም መያዝህ ወደ በሩ ከመሄደህ በፊት የተሰጡትን አቀራረቦች እንድትከልስ ያስችልሃል። የውጭ አገር ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሰዎችን ልታገኝ በምትችልባቸው ክልሎች ውስጥ ስትሠራ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን ምሥራች የተባለውን የእንግሊዝኛ ቡክሌት መያዝህ ጥሩ ነው። ለወጣቶች ተብለው ከተዘጋጁት ጽሑፎች አንዱን ቅጂ መያዝህ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆችን ለማነጋገር ዝግጁ እንድትሆን ይረዳሃል።

3 የምትጠቀምባቸውን ጽሑፎች ሁሉ በጥሩ ሁኔታ መያዝና በቦርሳህ ውስጥ ሥርዓታማ በሆነ መንገድ መቀመጥ አለባቸው። ቦርሳው የግድ አዲስ መሆን ባይኖርበትም ንጹሕና ያልተቀዳደደ መሆን አለበት። የአገልግሎት ቦርሳህ ምሥራቹን ለማወጅ ከምትጠቀምባቸው መሣሪያዎች አንዱ ነው። በጥሩ ሁኔታ ያዘው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ