ጽሑፎቼ በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?
ልናበረክተው ያሰብነውን የትኛውንም ጽሑፍ በተመለከተ ይህን ጥያቄ መጠየቃችን ተገቢ ነው። የተጣጠፈ፣ የተሻሸ፣ የቆሸሸ ወይም የተቀደደ ጽሑፍ ይዘን አገልግሎት መውጣታችን የይሖዋን ድርጅት ስም የሚያስነቅፍ ከመሆኑም ሌላ የምናነጋግረው ሰው በጽሑፉ ውስጥ ባለው ማራኪና ሕይወት አድን መልእክት ላይ እንዳያተኩር ያደርጋል።
ታዲያ ጽሑፎቻችንን በንጽሕና መያዝ የምንችለው እንዴት ነው? ብዙዎች የአገልግሎት ቦርሳቸውን ሲያደራጁ ተመሳሳይ ጽሑፎችን አንድ ላይ ማስቀመጥ ጠቃሚ ሆኖ አግኝተውታል። ለምሳሌ በቦርሳቸው ውስጥ ለመጻሕፍት፣ ለመጽሔቶችና ለብሮሹሮች እንዲሁም ለትራክቶችና ለሌሎች ጽሑፎች የተለያየ ኪስ ይጠቀማሉ። መጽሐፍ ቅዱሳቸውንና ሌሎች ጽሑፎቻቸውን ከተጠቀሙባቸው በኋላ ወደ ቦርሳቸው ሲመልሱ እንዳይበላሹ በጥንቃቄ ያስቀምጧቸዋል። አንዳንድ አስፋፊዎች ጽሑፎቻቸውን የሚይዙት በባይንደር ወይም ጽሑፍ ለመያዝ ተብለው በተሠሩ የፕላስቲክ መያዣዎች ነው። ጽሑፎቻችንን የምንይዝበት መንገድ ምንም ይሁን ምን ለሰዎች የተበላሸ ወይም የቆሸሸ ጽሑፍ በመስጠት በአገልግሎታችን ላይ እንከን እንዲያገኙ አንፈልግም።—2 ቆሮ. 6:3