የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/95 ገጽ 4
  • ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ ለማስተማር ይጠቅማል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ ለማስተማር ይጠቅማል
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ—አምላክ ለሰው ሁሉ መመሪያ እንዲሆን የሰጠው መጽሐፍ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ለመስክ አገልግሎት የሚሆኑ መግቢያዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • የአምላክ ቃል መመሪያ ይሰጣል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ እንዴት ማበርከት ይቻላል?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 11/95 ገጽ 4

ቅዱስ ጽሑፉ ሁሉ ለማስተማር ይጠቅማል

1 የመጽሐፍ ቅዱስን ዋጋማነት በተመለከተ የተለያዩ ብዙ ሐሳቦች ይሰጣሉ። ይሁን እንጂ እኛ የሰው ልጅ ላለበት ውስብስብ ችግሮች መፍትሄና በግለሰብ ደረጃ ለምንከተለው የሕይወት ጎዳና የሚሆን እምነት የሚጣልበት መመሪያ በውስጡ እንደያዘ እናምናለን። (ምሳሌ 3:5, 6) መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ምክር የያዘው ጥበብ አቻ የለውም። በውስጡ የያዛቸውን ሥነ ምግባራዊ የአቋም ደረጃዎች የሚወዳደራቸው የለም። ‘የልብን ስሜትና ሐሳብ ለመመርመር የሚችል’ ኃይለኛ መልእክት አለው። (ዕብ. 4:12) ሰዎች ይህንን መጽሐፍ ከመጽሐፍ መደርደሪያ ላይ አንስቶ በጥሞና የመመርመሩን አስፈላጊነት እንዲገነዘቡ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው? በታኅሣሥ ወር ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ስታበረክት ከሚከተሉት መግቢያዎች ውስጥ አንዳንዶቹን ለመጠቀም ትፈልግ ይሆናል።

2 ብዙ ሰዎች በቤተሰብ ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮች ስለሚያሳስቧቸው የሚከተለው አቀራረብ ትኩረታቸውን ይስብ ይሆናል:-

◼ “በዛሬው ጊዜ የማነጋግራቸው አብዛኞቹ ሰዎች በቤተሰብ ውስጥ ያሉ ችግሮች ስለሚያሳስቧቸው በጣም ተጨንቀዋል። እንደዚህ ላሉ ጉዳዮች ከሁሉ የተሻለ ምክር ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ ችግሮችን ለማስወገድ ወይም ለመፍታት የሚረዳ ተግባራዊ ምክር ይሰጣል። አንድ ምሳሌ ላሳይዎ።” ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 238–247 ካሳየኸው በኋላ መጽሐፉን ለቤቱ ባለቤት አበርክትለት።

3 በሚከተለውም መግቢያ ልትጠቀም ትችላለህ:-

◼ “ጋዜጣ ባነበብን ወይም ዜና ባዳመጥን ቁጥር ከዚህ በፊት ያልሰማነው ጭንቀት የሚፈጥር ሌላ አሳሳቢ ችግር እንሰማለን። [በቅርቡ በዜና ማሰራጫዎች የቀረቡ አንዳንድ አሳሳቢ ጉዳዮች ጥቀስ።] እንደነዚህ ያሉ ችግሮችን መወጣት የምንችለው እንዴት ነው? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] በ1983 የወቅቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የነበሩ አንድ ሰው [ሮናልድ ሬገን] መጽሐፍ ቅዱስ እስካሁን የተጻፉ መጽሐፎች ከያዙት የሚበልጥ መልእክት በውስጡ እንዳለና ‘ሰዎች ላሉባቸው ማንኛውም ችግሮች መፍትሔ እንደያዘ’ ተናግረው ነበር። የተናገሩት ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ የሚለውን ያስታውሰናል። [2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17⁠ን አንብብ።] መጽሐፍ ቅዱስ ልንተማመንበት የምንችለው ለምን እንደሆነ ላሳይዎ።” መጽሐፍ ቅዱስን ማመን የሚችሉት ለምንድን ነው? በተባለው ትራክት አለዚያም ለዘላለም መኖር በተባለው መጽሐፍ ገጽ 56 ውስጥ ያሉትን አንዳንድ ጎላ ያሉ ነጥቦች ግለጽ። ሌላ ጊዜ ተመልሰህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ እየተከናወኑ ባሉት ክስተቶች እንዴት በአስደናቂ ሁኔታ እየተፈጸሙ እንዳሉ ለመወያየት እንድትችሉ ሐሳብ አቅርብለት።

4 በክልልህ ውስጥ ብዙ ሃይማኖት የለሽ ሰዎች የሚኖሩ ከሆነ የሚከተለውን አቀራረብ ልትጠቀም ትችላለህ:-

◼ “ብዙ ሰዎች አንዳንድ ቅዱሳን መጻሕፍት እርስ በርሳቸው እንደሚጋጩና በተረት ብቻ የተሞሉ እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ። በሃይማኖት ስም በጣም ብዙ መጥፎ ነገሮች ሲከናወኑ ስለተመለከቱ ሌላው ቀርቶ በመጽሐፍ ቅዱስ እንኳ አያምኑም። እንዲያውም በጣም ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? ብለው ራሳቸውን ይጠይቃሉ። እርስዎስ ምን ሐሳብ አለዎ?” መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። የሰውዬውን ምላሽ አይተህ ለዘላለም መኖር መጽሐፍ ምዕራፍ 5 አውጣና በአንድ ወይም በሁለት ነጥቦች ላይ አወያየው። በተጨማሪም ገጽ 57 ላይ በሚገኘው “ኢየሱስ ክርስቶስ ከአምላክ የተላከ ነበርን?” በሚለው ርዕስ ውስጥ ባሉት አንቀጽ 1 እና 2 መጠቀሙ ጥሩ የሚሆንበት ጊዜ አለ።

5 ታላቁ አስተማሪያችን መማር የሚፈልጉ ሁሉ የፈቃዱን እውቀት እንዲያገኙ ዝግጅት አድርጓል። ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ዋጋማነት እንዲገነዘቡ መርዳት እነርሱን ለመርዳት ልናደርጋቸው ከምንችላቸው ከሁሉ የተሻሉ ነገሮች አንዱ ነው፤ ሕይወታቸውን ሊያተርፍላቸው ይችላል።— ምሳሌ 1:32, 33

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ