መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥር. 1
“አንዳንዶች የተመቻቸ ኑሮ ሲኖሩ ሌሎች ግን የዕለት ጉርስ ለማግኘት ብዙ የሚደክሙት ለምን እንደሆነ አስበው ያውቃሉ? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ የሚናገረው ነገር አለ። [ኢዮብ 34:19ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክ የኑሮ ልዩነት የማይኖርበት ጊዜ እንደሚያመጣ ይናገራል።”
ንቁ!® ጥር 2002
“ብዙውን ጊዜ መጠነ ሰፊ የሆነ አሳዛኝ አደጋ ሲደርስ በዚያ ሁሉ መሃል ድፍረትና ራስን መሥዋዕት የማድረግ መንፈስ ስላሳዩ ሰዎች የሚገልጹ አስደሳች ዘገባዎች እንሰማለን። በቅርቡ በኒው ዮርክ ከደረሰው አደጋ ጋር በተያያዘ እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ተፈጽሞ ነበር። ብዙዎች በምሳሌ 3:27 ላይ የተገለጸውን ዓይነት መንፈስ አሳይተዋል። [አንብበው።] ይህ የንቁ! መጽሔት ከአደጋው ከተረፉት ሰዎች መካከል ከአንዳንዶቹ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስና በግለሰብ ደረጃ ልናስብባቸው የሚገቡ ከአደጋው ጋር በተያያዘ ጎልተው የተንጸባረቁ አንዳንድ ነጥቦችን ይዟል።”
መጠበቂያ ግንብ ጥር. 15
“ብዙ ሰዎች ምስሎችን ለአምልኮ ይጠቀሙባቸዋል። እንደ እነዚህ ያሉት ነገሮች የማዳን ኃይል ያላቸው ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] እውነተኛው አምላክ ምን እንደሚያደርግልን እባክዎ ይመልከቱ። [ራእይ 21:3, 4ን አንብብ።] ይህንን ማከናወን የሚችለው እውን የሆነ አምላክ ብቻ ነው። ይህ መጽሔት የዚህን እውን አምላክ ማንነትና በሱ ላይ ትምክህት በማሳደር መጠቀም የምንችልበትን መንገድ ይጠቁማል።”
Jan. 22
“አብዛኞቻችን የምንኖርበት ቤት ያለን መሆኑን እምብዛም በአድናቆት አናስበው ይሆናል። በዓለም ዙሪያ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ስደተኞች ግን የሚናፍቁትን የተረጋጋ ሕይወት ሳያገኙ እንዲሁ ይባዝናሉ። ይህ የንቁ! መጽሔት የዚህን ችግር መንስኤና መጽሐፍ ቅዱስ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ቤት ስለሚያገኝበት ጊዜ የሚናገረውን ተስፋ ያብራራል።”