መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1
“ስለ አካባቢ ብክለት ብዙ ሲነገር እንሰማለን። ይሁን እንጂ አእምሮም ሊበከል እንደሚችል አስበው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ በአካላዊም ሆነ በመንፈሳዊ ንጹህ መሆን እንዳለብን ጠበቅ አድርጎ ይገልጻል። [2 ቆሮንቶስ 7:1ን አንብብ።] በዚህ መጽሔት ላይ ጠቃሚና ተግባራዊ ሐሳብ ያገኛሉ።”
ንቁ! የካቲት 2002
“መጽሐፍ ቅዱስ ማንም ሰው ‘ታምሜአለሁ’ የማይልበት ጊዜ እንደሚመጣ ተስፋ ይሰጣል። [ኢሳይያስ 33:24ን አንብብ።] ከዚህ ትንቢት ጋር በመስማማት ይህ የንቁ! እትም በሚልዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችንና አረጋውያንን ስለሚያሠቃይ በሽታ ይናገራል። ርዕሱ ‘በአርትራይተስ የሚሠቃዩ ሰዎች ያላቸው ተስፋ’ ይላል። ጥሩ ትምህርት እንደሚያገኙበት ተስፋ አደርጋለሁ።”
መጠበቂያ ግንብ የካቲት. 15
“ሕይወትዎን በተሻለ መንገድ እንዴት መምራትና ትላልቅ ውሳኔዎችን እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ አስበው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] እንደ ወርቃማው ሕግ ያለ ከሁሉ ተሻለ መመሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል። [ማቴዎስ 7:12ን አንብብ።] እኛን በቀጥታ ሊጠቅሙን የሚችሉ ምን ሌሎች አምላካዊ መመሪያዎች አሉ? መልሱን በዚህ መጽሔት ውስጥ ያገኛሉ።”
Feb. 22
“ብዙ የሥራ ቦታዎች አደገኛ እየሆኑ እንደመጡ አስተውለው ይሆናል። ይህ መጽሔት የሥራ ቦታዎች አደጋ የማያስከትሉ እንዲሆኑ ማድረግ ስለሚቻልባቸው መንገዶች ጥሩ ሐሳቦችን ያቀርባል። ከዚህም በላይ ደህንነታችን ለሰብዓዊ ሥራ ሚዛናዊ አመለካከት በመያዛችን ላይ የተመካ እንደሆነም ያመለክታል። ወስደው ያነብቡታል?”