መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
“ብዙ ሰዎች በምድር ላይ ሰላም ሰፍኖ ለማየት ይመኛሉ። ይህ ጥቅስ የሚፈጸምበት ጊዜ የሚመጣ ይመስሎታል? [መዝሙር 46:9ን አንብብ። መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ጥቅሱ እንዴት እንደሚፈጸምና አምላክ ከምድር ጦርነትን ለመሻር በገባው ቃል ላይ ትምክህት ማሳደር የምንችልበትን ምክንያት ያብራራል።”
ንቁ! ጥር 2004
“ብዙ ገበሬዎች በግብርና መተዳደር እየከበዳቸው እንደመጣ ሲነገር ሰምተው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ የንቁ! እትም ይህን ችግር በተመለከተ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ወደፊት የተሻለ ጊዜ እንደሚመጣ ስለሚሰጠው ተስፋ ማብራሪያ ይዟል። [መዝሙር 72:16ን አንብብ።] ተመልሼ በምመጣበት ጊዜ አምላክ ይህን የሚፈጽመው እንዴት እንደሆነ ብነግርዎት ደስ ይለኛል።”
መጠበቂያ ግንብ ጥር 15
“በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች ቃላቸውን የማይጠብቁ በመሆናቸው በሰው ላይ እምነት መጣል አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። በሰጠው ተስፋ ላይ እምነት ልናሳድርበት የምንችል አካል ይኖራል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ኢያሱ 23:14ን አንብብ።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሚገኙት አምላክ የሰጣቸው ተስፋዎች ላይ እንዴት እምነት ማሳደር እንደምንችል ይገልጻል።”
Jan. 22
“የአምላክ የግል ስም በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲጻፍ ይህን ይመስላል። [ሽፋኑን አሳየው።] አንዳንድ ሰዎች ስሙን ፈጽሞ መጥራት የለብንም የሚል አስተሳሰብ አላቸው። ሌሎች ደግሞ በስሙ በስፋት ይጠቀማሉ። ይህ የንቁ! እትም ይህን አወዛጋቢ ጉዳይ ይመረምራል። ከዚህ በተጨማሪ አምላክን በስሙ ማወቅ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።” መዝሙር 83:18ን አንብብ።