መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 1
“አብዛኞቻችን ዛሬ በሰዎች ላይ የሚደርሱትን ነገሮች ስንመለከት ወደፊት ምን ይመጣ ይሆን? ብለን እናስባለን። ኢየሱስ ክርስቶስ በሰፊው በሚታወቀው ጸሎቱ ላይ የወደፊቱን ጊዜ በእርግጠኝነት ለመመልከት የምንችልበትን ምክንያት ገልጿል። [ማቴዎስ 6:9, 10ን አንብብ።] የሰው ልጅ ከረዥም ጊዜ በፊት የተፈጸሙ ስህተቶችን እየደገመ ነው። ሆኖም በእነዚያ ጊዜያት አምላክን ያገለግሉ የነበሩ ሰዎች አስደሳች የወደፊት ተስፋ ነበራቸው። ይህ መጽሔት እኛም በተመሳሳይ ስለ ወደፊቱ ጊዜ አስደሳች ተስፋ እንዴት ማግኘት እንደምንችል ያሳያል።”
ንቁ!® መጋቢት 2002
“ጋብቻዎች አስደሳች ጅምር ቢኖራቸውም አብዛኞቹ በፍቺ እንደሚደመደሙ ሳያስተውሉ አይቀሩም። ይህ የንቁ! መጽሔት ጋብቻን ዘላቂና አስደሳች ማድረግ ስለሚቻልበት መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ሐሳብ ስለሚያብራራ ልሰጥዎ እፈልጋለሁ።”
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 15
“ጽድቅ የሰፈነበት አገዛዝ ይህችን ምድር የተሻለች የመኖሪያ ቦታ ያደርጋታል ቢባል ይስማማሉን? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] እባክዎ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ተስፋ ይመልከቱ። [መዝሙር 37:11ን አንብብ።] በዚህ መጽሔት ውስጥ በተገለጸው ፍጹም መሪ ግዛት ሥር እንዲህ ያለውን ሰላም ማግኘት እንችላለን።”
Mar. 22
“የመሬት መንቀጥቀጥ ይህ ነው የማይባል ጥፋትና ሞት ሊያደርስ ይችላል። የእልቂቱ ተራፊዎች ባብዛኛው የሚጠለሉበት ቤትም ሆነ መቋቋሚያ የሚሆናቸው ምንም ነገር አይኖራቸውም። ይህ የንቁ! እትም የእልቂቱ ሰለባዎች ከመሬት መንቀጥቀጥ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን እንዴት መቋቋም እንደቻሉ ይናገራል። ከዚህም በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ አንድ በጣም አስፈላጊ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ ክፍል የሆነው እንዴት እንደሆነም ያብራራል።”