መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1
“በጠና የታመመ ወይም የአካል ጉዳት የደረሰበት የሚያውቁት ሰው አለ? እነዚህ ሰዎች ማበረታቻ ያስፈልጋቸዋል ቢባል እንደሚስማሙ ምንም ጥርጥር የለውም። ሆኖም ምን ብለን ልናበረታታቸው እንችላለን? መጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ያዘለ ሐሳብ ይዟል። [ኢሳይያስ 35:5, 6ን አንብብ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ይህ ትንቢት እንደሚፈጸም እርግጠኞች ልንሆን የምንችልበትን ምክንያት ያብራራል።”
ንቁ! ግንቦት 2002
“በዚህ ባሳለፍነው ዓመት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የዓለም ሰላም ተናግቷል። ሰብዓዊ መንግሥታት ለዓለም ሰላም ማምጣት የሚችሉ ይመስልዎታል? [መልሱን ካዳመጥክ በኋላ ኢሳይያስ 2:4ን አንብብ።] ይህ የንቁ! እትም ዓለም አቀፍ ሰላም በቅርቡ እውን ሊሆን እንደሚችል እርግጠኞች መሆን የምንችልበትን ምክንያት ይናገራል።”
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 15
“አምላክን ማወቅ የሚቻል ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] በደንብ የማናውቀውን ሰው ማመን እንደሚያስቸግረን የታወቀ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ አምላክን እንድንፈልገው የሚያበረታታን ለዚህ ነው። [ሥራ 17:26, 27ን አንብብ።] እነዚህ ርዕሶች አምላክን ይበልጥ ማወቅ እንዴት እንደሚቻል ይነግሩናል።”
May 22
“የዓለም መሪዎች ችግሮቻችንን ለማስወገድ የተለያዩ ሙከራዎች አድርገዋል። አንዱ አዲስ ሙከራ ግሎባላይዜሽን ተብሎ ይጠራል። ይህ አዲስ ሙከራ ሕይወትዎን እንዴት እየነካው እንዳለ በዚህ መጽሔት ውስጥ ተብራርቷል። ከዚህም በላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ መፍትሔ እንደሚመጣ የሚናገረውን ትንቢትም ማንበብ ይችላሉ።” ከዚያም ማቴዎስ 6:9, 10ን አንብብ።