የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/03 ገጽ 5
  • አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • የ2010 የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 4/03 ገጽ 5

አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም

1 መገናኛ ብዙኃንና በማስተማሩ ሙያ የተሰማሩ ሰዎች ለቁሳዊ ብልጽግና ከፍተኛ ቦታ የሚሰጡ ቢሆንም የአምላክ ቃል ግን የሚመክረን ‘በመልካም ሥራ ባለ ጠጎች እንድንሆን’ ነው። (1 ጢ⁠ሞ. 6:18) ከግንቦት 2003 ጀምሮ የሚካሄደው የልዩ ስብሰባ ፕሮግራም ጭብጥ ይህ ይሆናል። በዚህ ስብሰባ ላይ ምን ማበረታቻ እናገኛለን?

2 የወረዳ የበላይ ተመልካቹ “በአምላክ ዘንድ ባለ ጠጋ ሁኑ” ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ያብራራል፤ እንዲሁም በመንፈሳዊ ባለ ጠጋ ለመሆን ጥረት ለሚያደርጉ አንዳንድ አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ ያደርጋል። ጎብኚ ተናጋሪው በዕለቱ በሚያቀርበው የመጀመሪያ ንግግር ላይ “በዚህ የመከር ወቅት የሚከናወኑ መልካም ሥራዎች” በሚል ርዕስ የአምላክ ሕዝቦች እያከናወኗቸው ያሉትን ሥራዎች ይገልጻል። እያንዳንዳችን ዛሬ እየተከናወነ ባለው ከአምላክ በተቀበልነው የመከር ሥራ ከበፊቱ የበለጠ በተሟላ መልኩ ተሳትፎ ማድረግ የምንችልበትን መንገድ እንድንመረምር ማበረታቻ እናገኛለን።

3 ክርስቲያን ወጣቶች በመንፈሳዊ ባለ ጠጎች ለመሆን የሚያደርጉትን ጥረት መመልከታችን በጣም ያስደስተናል! ይህ ይሖዋን የሚያስከብር ከመሆኑም በላይ ወደፊት ሌሎች የአገልግሎት መብቶች ላይ ለመድረስ የሚያስችል ጥሩ መሠረት ይሆንላቸዋል። “ይሖዋን በማወደስ ላከናወኑት መልካም ሥራ ወጣቶችን ማመስገን” የሚለው ንግግር በወረዳው ውስጥ ያሉት ወጣት ክርስቲያኖች ያከናወኑትን መልካም ሥራ ያጎላል።

4 መልካም ሥራዎችን ማከናወን ምን ውጤቶች ያስገኛል? ጎብኚ ተናጋሪው “መልካም ሥራ መሥራታችሁን ቀጥሉ፤ የይሖዋንም በረከት እጨዱ” በሚለው የመደምደሚያ ንግግሩ ላይ የዚህን መልስ ይሰጠናል። የተትረፈረፈ በረከት የምናጭድባቸውን አራት ዘርፎች የሚያብራራ ሲሆን እነዚህም:- (1) በግለሰብ ደረጃ፣ (2) በቤተሰብ ደረጃ፣ (3) በጉባኤ ደረጃ እንዲሁም (4) በዓለም ዙሪያ በድርጅት መልክ የምናገኛቸው በረከቶች ናቸው።

5 ራሳቸውን ለይሖዋ የወሰኑ ሰዎች በስብሰባው ላይ የመጠመቅ አጋጣሚ ያገኛሉ። ይህንን እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅተህ ከሆነ ለሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ሳትዘገይ ንገረው።

6 ጉባኤያችሁ ስብሰባውን የሚያደርግበት ቀን በማስታወቂያ ሲነገር በስብሰባው ላይ ለመገኘት ወዲያውኑ ፕሮግራም አውጣ። በመክፈቻው መዝሙርና ጸሎት መካፈል እንድትችል ቀደም ብለህ ለመድረስ ጥረት አድርግ። በልዩ ስብሰባው ቀን መገኘታችንና ፕሮግራሙን በአጠቃላይ በትኩረት መከታተላችን በአምላካችን በይሖዋ ዘንድ ባለ ጠጋ የሚያደርገንን ጎዳና ይዘን እንድንቀጥል ያጠናክረናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ