መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 1
“የተሳካ ኑሮ ያላቸው የሚመስሉ ሆኖም በሕይወታቸው ውስጥ እርካታ የሌላቸው ሰዎችን ያውቁ ይሆናል። እነዚህ ሰዎች እንዲህ የሚሰማቸው ምን ጎድሏቸው ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥህ ጠብቀው። ከዚያም ማቴዎስ 5:3ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ውስጣዊ ሰላም ለማግኘት የሚረዳን ዋነኛው ቁልፍ መንፈሳዊ ፍላጎታችንን ማርካት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ሐምሌ 2005
“ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሰዎች በላቀ ሁኔታ የሚታወቅ ቢሆንም ብዙ ሰዎች ማንነቱን በተመለከተ ጥያቄ ያነሳሉ። የኢየሱስ ሐዋርያት እንኳ እንዲህ ያለ ጥያቄ አንስተው እንደነበር ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥህ ጠብቀው። ከዚያም ማርቆስ 4:41ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የኢየሱስን ትክክለኛ ማንነት በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 15
“የሰው ዘር ባሳለፋቸው በሺህ የሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ ብዙ ሃይማኖታዊ ትምህርቶች ተፈጥረዋል። ከእነዚህ መካከል የትኞቹ ትክክል የትኞቹ ደግሞ ሐሰት እንደሆኑ መለየት የሚቻል ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥህ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት አምላክን የሚያስደስቱ እውነተኛ ትምህርቶች ምንጫቸው ምን መሆን እንዳለበት የሚናገር ሐሳብ ይዟል።” 2 ጢሞቴዎስ 3:16ን አንብብ።