መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1
“ወላጆች ልጃቸውን በሞት መነጠቃቸው ጊዜ የማይሽረው መሪር ሐዘን ያስከትልባቸዋል። እነዚህ ወላጆች ማጽናኛ ማግኘት የሚችሉት ከየት ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ሮሜ 15:5ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክ፣ ሐዘን ለደረሰባቸው ወላጆች ማጽናኛ የሚሰጥባቸውን አንዳንድ መንገዶች ያብራራል።”
ንቁ! ግንቦት 2007
“አምላክ የምናደርጋቸውን ነገሮችና የመጨረሻ ዕድላችንን አስቀድሞ ወስኗል ብለው ያስባሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ መሠረት አምላክ ሰዎች ሕይወታቸውን መምራት የሚፈልጉበትን መንገድ በተመለከተ የራሳቸውን ምርጫ እንዲያደርጉ ፈቅዶላቸዋል። [ዘዳግም 30:19ን አንብብ።] ይህ ርዕስ መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ምን እንደሚል ይናገራል።” ገጽ 12 ላይ ያለውን ርዕስ አሳየው።
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 15
“ለዚህ ጥያቄ ምን ምላሽ ይሰጣሉ? [በሽፋኑ ላይ ያለውን ጥያቄ አንብብና መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊቱን ጊዜ በተስፋ መጠበቅ የምንችልበትን ምክንያት ይነግረናል። [ማቴዎስ 6:9, 10ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የአምላክ መንግሥት የአምላክ ፈቃድ በምድር ላይ እንዲፈጸም የሚያደርገው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ሰኔ 2007
“በዚህ ጥቅስ ላይ ያለውን ሐሳብ በተመለከተ ምን አመለካከት እንዳለዎት ባውቅ ደስ ይለኛል። [1 ጢሞቴዎስ 6:10ን አንብብ።] ገንዘብንና ቁሳዊ ሀብትን የሚያሳድዱ ሰዎች ሥቃይ ይደርስባቸዋል ብለው ያምናሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት ሀብትን ማሳደድ የሚያስከትላቸውን መጥፎ ውጤቶች በተመለከተ ማብራሪያ ይሰጣል።”