የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/07 ገጽ 2
  • አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • መንፈሳዊነታችንን እንድንጠብቅ የሚረዳን የወረዳ ስብሰባ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
km 11/07 ገጽ 2

አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም

ይሖዋ ከፍተኛ ክብር ሊሰጠው የሚገባ አምላክ ነው። ይሁንና ክብር ልንሰጠው የምንችለው እንዴት ነው? በዚህ ረገድ አንዳንዶች ምን ተፈታታኝ ሁኔታዎች ያጋጥሟቸዋል? በአሁኑ ጊዜ ለይሖዋ ክብር እየሰጡ ያሉ ሰዎች ምን በረከት ያገኛሉ? የ2008 የአገልግሎት ዓመት የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ይሰጣል። ‘ሁሉንም ነገር ለአምላክ ክብር አድርጉት’ የሚል ጭብጥ አለው። (1 ቆሮ. 10:31) ስብሰባው በሚካሄድባቸው ሁለት ቀናት ውስጥ የሚቀርቡልን የተትረፈረፉ መንፈሳዊ ትምህርቶች በምን ነገሮች ላይ እንደሚያተኩሩ እስቲ እንመልከት።

የአውራጃ የበላይ ተመልካቹ “ለአምላክ ክብር መስጠት ያለብን ለምንድን ነው?” እና “አምላክ ያወጣቸውን መሥፈርቶች በማሟላት ምሳሌ ሁኑ” በሚሉ ርዕሶች ንግግር ያቀርባል። “ለአምላክ ክብር እየሰጡ ያሉት እነማን ናቸው?” የሚል ጭብጥ ያለውን የሕዝብ ንግግርም ሆነ “በዓለም ዙሪያ አንድ ሆኖ ለአምላክ ክብር መስጠት” የሚለውን የመደምደሚያ ንግግር የሚያቀርበው እሱ ነው። በተጨማሪም ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤትን ይመራል። የወረዳ የበላይ ተመልካቹ “የአምላክን ክብር በማንጸባረቅ ደስ ይበላችሁ” እና “ወረዳው ለሚያስፈልጉት ነገሮች ትኩረት መስጠት” የሚል ጭብጥ ያላቸውን ንግግሮች ያቀርባል፤ እንዲሁም በ 2 ጴጥሮስ 1:12 ላይ የተመሠረተውን “‘በእውነት ጸንታችሁ’ ኑሩ” የሚለውን ንግግር ይሰጣል። በተጨማሪም “የአቅኚነት አገልግሎት ለአምላክ ክብር ያመጣል” በሚል ጭብጥ ትምህርት ይቀርብልናል። ከዚህም በላይ በዚህ ስብሰባ ላይ ሁለት ስሜት ቀስቃሽ ሲምፖዚየሞች ይኖራሉ። የመጀመሪያው “በሁሉም የሕይወታችን ዘርፎች ለአምላክ ክብር መስጠት” የሚል ጭብጥ ያለው ሲሆን በ1 ቆሮንቶስ 10:31 ላይ የሚገኙት በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉ ቃላት ያላቸውን ጥልቅ ትርጉም ያብራራል። “ይሖዋን ለማወደስ ቅዱስ አገልግሎት ማቅረብ” የሚል ርዕስ ያለው ሁለተኛው ሲምፖዚየም ደግሞ የአምልኮታችንን የተለያዩ ገጽታዎች ይዳስሳል። ቅዳሜ ከሚከናወነው የጥምቀት ሥነ ሥርዓት በተጨማሪ እሁድ ዕለት የመጠበቂያ ግንብ ፍሬ ሐሳብና በዕለት ጥቅሱ ላይ ውይይት ሲደረግ የሚያሳይ ክፍል ይቀርብልናል።

አብዛኛው የሰው ዘር የአምላክን ሕልውና ለመቀበል ፈቃደኛ አይደለም። ብዙዎች ትኩረታቸው በሰብዓዊ ውጥኖች ከመከፋፈሉ የተነሳ ስለ ይሖዋ ክብር ማሰብ ተስኗቸዋል። (ዮሐ. 5:44) እኛ ግን ‘ሁሉንም ነገር ለአምላክ ክብር ማድረግ’ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ቆም ብለን ማሰባችን ጠቃሚ መሆኑን እናምናለን። በስብሰባው ላይ ለመገኘትና በአራቱም ክፍለ ጊዜያት ከሚቀርቡት ትምህርቶች ሙሉ ተጠቃሚ ለመሆን እቅድ እናውጣ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ