“እናንተ የእኔን ጽሑፍ ከወሰዳችሁ እኔም የእናንተን እወስዳለሁ”
በአገልግሎት ላይ የምናገኛቸው አንዳንድ ሰዎች እንዲህ የሚል ሐሳብ ያቀርቡልናል። መጽሐፍ ቅዱስ ለማጥናት የሚረዱትን ጽሑፎቻችንን የውሸት ትምህርት በሚያስተላልፉ ጽሑፎች እንደማንለውጥ የታወቀ ነው፤ ታዲያ በጥበብ መልስ መስጠት የምንችለው እንዴት ነው? (ሮም 1:25) እንዲህ ማለት እንችላለን፦ “ለግብዣው አመሰግናለሁ። ለመሆኑ ይህ ጽሑፍ የሰው ልጆች ላሉባቸው ችግሮች ምን የመፍትሔ ሐሳብ ያቀርባል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጡት። የጥያቄውን መልስ ለማግኘት ጽሑፉን እንድታነብቡት ከነገራችሁ ደግሞ እናንተ የያዛችሁትን ጽሑፍ እንዲወስድ የጋበዛችሁት በቅድሚያ ስለ ይዘቱ ከነገራችሁት በኋላ እንደሆነ ልትገልጹለት ትችላላችሁ። ከዚያም ማቴዎስ 6:9, 10ን አንብቡለት ወይም በቃላችሁ ጥቀሱለት።] ኢየሱስ የአምላክ ፈቃድ በምድር ላይ እንዲፈጸም የሚያደርገው የአምላክ መንግሥት መሆኑን ጠቁሟል። ስለዚህ የማነብባቸው መንፈሳዊ ጽሑፎች በሙሉ በዚህ መንግሥት ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ናቸው። የአምላክ መንግሥት በምድር ላይ ከሚያከናውናቸው ነገሮች መካከል አንዳንዶቹን ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ላሳይዎት?”